Sep 2022

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣የተጠሪ ተቋማትና የክልል ውሀና ኢነርጅ ቢሮዎች የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት እቅድ ለውይይት ቀረበ።

በባህር ዳር ከተማ ከመስከረም 13/2015ኣ.ም ጀምሮ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮዎች፤ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን አገልግሎት፤ የኢነርጅ ልማትንና የዉሃ ሀብት አስተዳደርን አስመልክቶ የ2015 ዓ.ም እቅዳቸውን ለውይይት አቅርበዋል።

የ2015 በጀት ዓመት የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እቅድ ዙሪያ ዉይይት እየተካሄደ ነው።

መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንዳሉት ባለፈዉ ዓመት በርካታ የውሃና ኢነርጂ ስራዎችን መሰራቱንን ገልጸው፤ ከ5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮዽያዉያንን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አውስተዋል።

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ፡፡

ፕሮጀክቱ የሚተገበረው ከአለም ባንክ በተገኘ 210 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን በ55 ወረዳዎች በውሀ አቅርቦት፤ በ67 ወረዳዎች ደግሞ በከርሰምድር ውሃ አለኝታ ጥናት ማድረግ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በ4 ወረዳዎች ላይ የመስኖ ልማት ስራዎችን ለመተግበር ያለመ ነው ፡፡

ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ የውሃ አጀንዳ አቅጣጫን ያስቀይራል

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ የዓባይ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ የኢትዮጵያን የመደራደር አቅም ከፍ ከማድረጉም በላይ ግድቡ እንዳይሠራ ሲጥሩ የነበሩ ኃይሎችን የ ”ውሃ መያዝ” አጀንዳ የሚያስቀይር ነው።  

የውሃ፣ የውሃ ዲፕሎማሲና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መማክርት ፎረም በባህር ዳር ተጀመረ።

ፎረሙም በዋነኛነት ከውሃ ሀብትና ከኢነርጂ ሀብት ልማት አንጻር፤ እንዲሁም ከሕዳሴው ግድብና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞቻችን ጋር በተያያዘ በዘርፉ ሙሁራን፤ በዘርፉ ተዋናዮችና በሚዲያ አካላት መካከል ሊሠሩ በሚገቡ ሥራዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ይመክራል፤

''የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር መልሶ ይከፍለናል'' ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

ክቡር ሚንስትሩ በትናንትናው ዕለት ከጉባኤው ጎን ለጎን በደቡብ ኮሪያ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ሥር ከሚገኘው የሀገሪቱ የከባቢ ኢንደስትሪ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት (Korea Environmental Industry and Technology Institute – KEITI) ምክትል ፕረዚደንት ሊ ዊዎንና የሥራ ኃላፊዎች ጋር በ

Aug 2022

ISA Ministerial and NFP level meeting held

H.E. Dr. Eng. Sultan Wali, state Minister of Energy Development welcomed the participants and expressed his admiration for ISA for their decision to organize the 4th International Solar Alliance forum

የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደ/ኮሪያ ውኃ ኮፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

ፕረዚደንቱ በስምምነት ንግግራቸው የኢትዮጵያና ኮሪያ ግንኙነት እንደማንኛውም ሀገር የዲፕሎማሲና የልማት ትብብር ብቻ ሳይሆን በደም የታተመ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በአጋርነት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኮሪያ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም ላይ ተሳተፉ ፤

ክቡር ሚኒስተርሩ ፎረሙ በይፋ ከከፈቱት ከቀድሞ የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ጋር ተገናኝተው በአካባቢ ጥበቃና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተነጋገሩ ሲሆን በተመሳሳይ ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዳይሬክተር ጃሚል አህመድ ጋር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምና አካባቢ ጥበቃ ሥራ ተወያይተዋል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመስክ ተሸከርካሪዎችን አከፋፈለ፡፡

በርክክብ መርሃ-ግብሩ ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት ዛሬ ርክክብ የሚፈጸምባቸው የመስክ ተሸከርካሪዎች በየክልሎቹ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት ቢሮዎች በአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ለሚገነቡ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ የተደረገ ነው

ስደተኞችንና የሚኖሩበትን አካባቢ ማህበረሰብ የማብሰያ ሀይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ስትራቴጂ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡

በስትራቴጅው ላይ የተደረገውን ውይይት የመሩት የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ እንደገለጹት ስደተኞችንና የአካባቢው ማህበረሰቦችን የሀይል አቅርቦት ታሳቢ አድርጎ ስትራቴጀው መዘጋጀቱን አድንቀውና ወደ ተግባር የመቀየር አስፈላጊነትን ገልጸው፤ ለስትራቴጅው ተፈጻሚነት ሚኒስቴር መስሪያ

Jul 2022

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተሻሻሉ ምድጃዎችን በሀገሪቱ ለማስራጨት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተሻሻሉ ምድጃዎችን በሀገሪቱ ለማሰራጨት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ይፋ አደረገ፡፡ ፕሮጀክቶቹ የቤት ውስጥ የማብሰያ ምድጃ ማሻሻያ ፕሮጀክትና የአረንጓዴ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች በቦሌ ክፍለ ከተማ ፒኮክ ፖርክ ችግኝ ተከላ አካሄዱ

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ባሻገር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት በዕለቱ የአረጋውያንና አቅመ ደካማ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ 10 ቤቶችን ግንባታ ለማከናወን ከቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ቦታዎችን ተረክቧል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጡ መሣሪያዎችን በድጋፍ አገኘ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 7 ሚሊየን ብር የሚያወጡ መሣሪያዎችን በድጋፍ አገኘ፡፡ መሣሪያዎች የወንዝ ፍሰት መጠንን፣ የከርሰ ምድር ውሃ ከፍታን ፣ የአፈር እርጥበት መጠንን፣ የውሃ ጥራትን እንዲሁም የሜትሮሎጂ መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደ ማዕከል በራሳቸው ማስተላለፍ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል፡፡

Jun 2022

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን በማስፈን የሀገሪቱን የውሃ ሀብት ለዜጎች ጠቀሜታ እንዲውል ማድረግ

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን በማስፈን የሀገሪቱን የውሃ ሀብት ለሀገሪቱ ዜጎች ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እንዲውል ማድረግ ይገባል ሲሉ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ ተናግረዋል፡፡

የሶላር ኢነርጂን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በተሰሩ ሥራዎችና ውጤቶች ዙርያ ባሳለፍነው ሳምንት ውይይት ተደረገ፡፡

ባለፉት አራት ዓመታት ሶላር ኢነርጂን በኢትዮጵያ ለማስፋፋትበተደረገውእንቅስቃሴድርጅቱ በተለይም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶች ከሚመረቱበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ከመጫናቸው በፊት የተስማሚነት ማረጋገጫአሰራር መዘርጋቱ፣ የሶላርቴክኖሎጂ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ቀረጥእንዲዘጋጅ ማደረጉና ከወርልድ

የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መማክርት ፎረም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ተካሄደ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምሁራንና ባለሙያዎች በመድረኩ ላይ ታድመዋል፡፡

እንቦጭን በነባር የውሃ እጽዋት ለመተካት የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ::

በዝዋይ /ደምበል ሐይቅ በእንቦጭ የተወረረውን የውሃ ዳርቻ በነባር የውሃ ዳርጃ እጽዋት ለመተካት የሚያስችል ስልጠና በባቱ ከተማ ተሰጠ፡፡ ስልጠናው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ አረንጓዴ እድገት ተቋም፣ ከአካባቢ ብዝኀ ሕይወትና የአየር ንብረት ለውጥ ፎረም ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ105 ሚሊየን ብር የተገዙ 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አከፋፈለ ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ105 ሚሊየን ብር የተገዙ 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አከፋፈለ፡፡ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የርክክብ ፕሮግራም ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ቁልፎቹን ለክልሎቹ ተወካዮች አስረክበዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ የጀመርን የአየር ንብረት እና ኢነርጂ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ቲዎልከንን ተቀብለው አነጋገሩ::

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ የጀመርን የአየር ንብረት እና ኢነርጂ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ቲዎልከንን ተቀብለው አነጋገሩ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወጎኖች ሰብዓዊ ድጋፍ አደረገ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተርጫ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡ በርክክቡ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የጀርመን - አፍሪካ የሃይል (ኢነርጂ) ትስስር ጉባኤ በሀምቡርግ ከተማ ተካሄደ፡፡

15ኛው የጀርመን - አፍሪካ የሃይል (ኢነርጂ) ትስስር ጉባኤ  በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በየዓመቱ እ.ኤ.አ በሰኔ ወር መግቢያ ላይ በጀርመን የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የግል ኩባንያዎች ጥምረት (አፍሪካ ፈራይን - Africa – Verein) እና በጀርመን መንግስት የኢኮኖሚ ጉዳዮችና አየር ንብ

May 2022

የባዮፊዉል ልማትን ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ

የባዮፊዉል ልማትን ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ዉይይት ተካሄደ፡፡ በዉይይቱ ላይ ከዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ፣ ከክልሎች የኢነርጂ ዘርፍ፣ ከመንግሥትና የግል ልማት ድርጅቶች ፣ከዩኒቨርሲዎችና ከምርምር ተቋማት የመጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ሃላፊዎችና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ከሂዋዌ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ለማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን መሠረተ ልማቱን ማዘመንና የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብና አሠራሩን በማቀላጠፍ መሠረተ ልማቶች ለማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያዩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር ለማዘመን ስምምነት ተፈራረመ ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ20 ከተሞችን የውሃ አገልግሎቶች አሠራር የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓትን በማስፈን ለማዘመን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱም በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተቃቀፉ 22 ከተሞች በ20ዎቹ ተግባራዊ የሚሆን ነው፡:

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አልያንስ (ISA) ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ::

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከISA ጋር የተፈራረመው አብሮ የመሥራት ስምምነት ከፀሐይ የሚገኝ ኃይልን በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋልና ዜጎችን የንጹሕ፣ ታዳሽና አስተማማኝ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱም ወቅት የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስት ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሱልጣን ወሊ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በፀሐይ ኃይል የታ

የመጪው ክረምት ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ይፋ ሆነ::

በብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትና አጋር አካላቱ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀ ወርክሾፕ ላይ ከክረምቱ ወቅት የአየር ፀባይ አዝማሚያ ትንበያ በተጨማሪ ያለፈው በልግ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ከነባራዊው አየር ጠባይ ጋር የነበረው ተመሳስሎም ግምገማም ተካሄዷል፡፡

Mar 2022

Feb 2022