የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር መረጃ አያያዝ ስርዓት /ICSMIS/ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር መረጃ አያያዝ ስርዓት /ICSMIS/ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡   ጥር 22/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ከኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን /አይ.ቲ/ ስራ አስፈፃሚ ጋር በጋራ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር መረጃ አያያዝ ስርዓት /Integrated Civil Service Management Information System/ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ለተቋሙ ለአመራሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡   ስልጠናውን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ መለሰ መንግስቱ የICSMIS ስልጠና ከዚህ በፊት ለባለሞያዎች በየደረጃው መሰጠቱን አስታውሰው፤ አመራሩ የግሉን መረጃ ለማየት፣ ከሰው ሃብት የሚፈለጉ አገልግሎቶችን ለማግኘትና በስራቸው ያሉትን የባለሞያዎችን ፍቃድ እንዴት ማፅደቅ ይቻላል የሚለውን የሚያስረዳ በመሆኑ ግልፅ ያልሆነውን በጥያቄ ለማዳበር ተሳታፊዎች በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡   ተቋሙ ወደሪፎርም ትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ በመሆኑ፤ በዲጅታል የአሰራር ስርዓት ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በተቋሙ እየተሰራ ያለው የሪፎርም አካል በመሆኑ በቀጣይ ወረቀት አልባ የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትም ያግዛል፡፡   ስልጠናውን የሰጡት በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በ ICSMIS የአይ.ቲ ሰፖርተር የሆኑት አቶ ጅክሳ እና አቶ ቸርነት የICSMIS ምንነትን አስፈላጊነትንና ጠቀሜታን ለሰልጣኞች ግልፅ ካደረጉ በኃላ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር መረጃ አያያዝ ስርዓት ዋናው አላማ የመረጃ ጥራትን ማሻሻል፣ ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት፣ ግልፀኝነት እና ውሳኔ አሰጣጥን ማሻሻል ነው ብለዋል፡፡   ተቋሙ ወደሪፎርም ትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ በመሆኑ፤ በዲጅታል የአሰራር ስርዓት ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በተቋሙ እየተሰራ ያለው የሪፎርም አካል በመሆኑ በቀጣይ ወረቀት አልባ የአሰራር ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትም ያግዛል፡፡   በስልጠናው የተቋሙ ስራ አስፈፃሚዎች፣ አማካሪዎች፣ ዴስኮችና የቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በሲስተሙ አጠቃቀም ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

Share this Post