የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ በመሆናችን ደስተኛ ነን።
==============================
የሉኮ አባያ ዙሪያ የመሬራ ቀበሌ ነዋሪዎች
ሉኮ አባያ፡-ጥር 28/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በጋራ ያስገነባውን የመሬራ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ይፋ ባደረገበት መርሃግብር ላይ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገለፁ።
መብራትን ከማገዶ ሲጠቀሙ መቆየታቸውንና በፕሮጀክቱ ኑሯቸው ወደአዲስ የአኗኗር ዘይቤ የተቀየረ እንደሆነ የገለፁት የአካባቢው ነዋሪ አቶ አሰፋ ሆራቶ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆናችን በሰው ጉልበት ሲሰሩ የነበሩ ስራዎችንም በኤሌክትሪክ መስራት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ለአባይ ግድብ የገዛነው ቦንድ ዛሬ በየቤታችን ክሶናል ያሉት ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ አቶ ረጋሳ ቡሪሳ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ በመሆናችን ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት ችለናል፤ ለዚህም እገዛ ያደረጉትን አመስግነዋል።
የ12ኛ ክፍል ተማሪ ባዩሽ ጃጃ እስከዛሬ ድረስ በኩራዝ እያጠናች እንደነበር አስታውሳ፤ አሁን በየቤታችን መብራት ስላለን ለዘንድሮ ፈተና የሚያዘጋጀኝን አጋዥ መፅሐፍትንም ከኢንተርኔት ላይ ማግኘት በመቻሏን ገልፃለች።
የመሬራ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ 2,500 የሚሆኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ለአካባቢው ወጣቶችም የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው።