የውኃ እና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የአፍሪካ ልማት ባንክ ልኡክን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የካቲት26/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ.) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሉኡካኑን ባነጋገሩበት ወቅት ሚኒስቴር መ/ቤቱ አጋር ድርጅቶች ጋር እየተሰሩ ባሉ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከዚህ ጋር አያይዘውም የአፍሪካ ልማት ባንክ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በሚሰራቸው የውኃ እና ኢነርጂ ፕሮጀከቶች ፈንድ በመስጠት እየተሰሩ ያሉ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እና የሥርጭት ሥራዎችን አበረታች ለውጥ እያስገኙ መምጣታቸውን አብራርተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በማከል ሀገራችን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸው በተለይ በሀይሉ አቅርቦት የተጀመሩ ለውጦች የኢኮኖሚ እድገት እያስገኘ ፣ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የህብረተሰቡን የማምረት አቅም እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት ከአጋር ድርጂቶች ጋር ለመስራት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ መሆኑን የገለጹት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በዚህም በኢነርጂ ዘርፍ የተሰሩ ፖሊሲዎችን ከልሶ የግል ባለሀብቱን ተሳታፊነት መጨመር የልማት አጋሮች ጋር እየሰራ ያለ ሲሆን ዋናው የልማት አጋር የአፍሪካ ልማት ባንክ ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ማለትም በኢኮኖሚ፣ በማበራዊና እና በተለያዩ ዘርፎች እየደገፈ የሚገኝ ሲሆን ዋናው ውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ነውም ብለዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢነርጂ ዘርፍ ባለፉት አመታት እየደገፉ ከነበሩት ፕሮከጅቶች አጠቃላይ የሆነ ግምገማ በማድረግ ቀሪ ስራዎችን ቆጥሮ ለመለየት እና በቀጣይ ፕሮጀክቶቹ የሚጠናቀቁበትን ጊዜ ለማስቀመጥ የሚረዳ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
የልማት አጋሮችም በኢነርጂ ተደራሽነት ላይ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ላይ ያለውን ለውጥ አድንቀው ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጠልና መንግስት በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ አዳዲስ ፕሮጀከቶች ላይም አብረው ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።