275 ኪሎ ዋት ሀይል የሚያመነጨው የኑስተሪክ የሶላር ሚኒ ግሪድ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

275 ኪሎ ዋት ሀይል የሚያመነጨው የኑስተሪክ የሶላር ሚኒ ግሪድ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።   የካቲት 8/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በቆራሄ ዞን መርሲን ወረዳ በኑስትሪክ ከተማ ተገኝተው የፕሮጀክቱን ስራ መጀመር በይፋ አብስረዋል።   የኑስትሪክ የሶላር ሚኒ ግሪድ በ179 ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን የከተማዋን 900 መቶ የሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል። በእለቱ የክልል ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች የፕሮጀክቱን ስራ መጀመር አስመልክቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።   የመርሲን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ባስተላለፉት መልእክት የኑስተሪክ ከተማ ከዋናው የሀይል መስመር ርቃ የምትገኝ በመሆኗ የመብራት አገልግሎት ሳታገኝ መቆየቷን ገልጸው በአለም ባንክ በተገኘ የብድር ድጋፍ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ከተማዋ የ24 ሰዓት የመብራት ተጠቃሚ መሆን መቻሏ ትልቅ እድል ነው ብለዋል።   ማህበረሰቡም ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አካባቢውን በማልማት የልማቱ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ፕሮጀክቱን መጠበቅ ፣መንከባከብና በአግባቡ መገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

Share this Post