ከ212 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጭ የውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ212 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጭ የውል ስምምነት ተፈረመ።   የካቲት 26/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 212,280,466.91 ብር በሚሆን ወጪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዋን ዋሽ ፕሮግራም እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች መረጃን ዲጅታላይዝ ለማድረግ የሚያስችሉ እቃዎችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።   ስምምነቱን የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ከዘ ትረስት ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ከብራዘርስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ተፈራርመዋል።   ብራዘርስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሀርድ ዌር ሰርቨር ኮምፖነንቶችን በ4 ወራት ጊዜ ገዝቶ ለማቅረብ በ179,938,796.91 ብር ውል የወሰደ ሲሆን ዘትረስት ቴክኖልጂ ሶሉሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ደግሞ ዋይት ቦርድ ቲቪ ፣ኦል ኢን ዋን ፒቪ እና ኦዲዮ ዲቫይስስ ቲቪ በ32,341,669 ብር በ4 ወራት ጊዜ ለማቅረብ ውል ወስደዋል።   ውል የወሰዱ ድርጅቶች በተቀመጠው የ 4 ወራት የጊዜ ገደብ እቃዎቹን እንዲያቀርቡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል። የበጀት ምንጩ ከብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

Share this Post