19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች 19ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ። "ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን" በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረው 19ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንና ዘላቂ መግባባትን የሚያጠናክር የጋራ ዓርማችን በመሆኑ፤ የቀደሙ አባቶች ለሰንደቅ ዓላማው ክብርና ለሀገራቸው ሉዓላዊነት ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት የምንዘክርበት ዕለት ነው። ቀኑም በየአመቱ የሚከበረው ዜጎች ስለሰንደቅ ዓላማው ምንነትና ትርጉም የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስችላል። የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን 7ኛውን አገር አቀፍ የምርጫ በሰላም መጠናቀቅ፣ ሃገራዊ ምክክሩ እና የመንግስት ምስረታው በስኬት የተጠናቀቀበት ማግስት በመሆኑ ከወትሮው ለየት ያደርገዋል። 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሀገር ደረጃ በጥቅምት ወር መጃመሪያው ሰኞ በሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በተወካዮች ምክር ቤት፣ በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች እና ክልሎች በአንድ ቀንና በተመሳሳይ ሰዓት ተከብሯል፡፡ ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetikt

Share this Post