የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራም (OWNP-CWA Phase III) እና በውጤት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮግራም (ESWAP PforR) ቀረጻ ላይ ውይይት ተካሄደ

የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራም (OWNP-CWA Phase III) እና በውጤት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮግራም (ESWAP PforR) ቀረጻ ላይ ውይይት ተካሄደ

ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)-

በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የንጹህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ለማስፋፋት ያለመውን የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራም (OWNP-CWA Phase III) እና የኢትዮጵያ ዘላቂ የውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና ፕሮግራም (ESWAP) በውጤት ላይ በተመሠረተ የፋይናንስ ድጋፍ (PforR) ለማስፈጸም በሚደረገው የፕሮግራም ቀረጻ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ።

ከህዳር 7 እስከ 11/2019 ዓ.ም የሚቆየው የሥራ ተልዕኮ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማትና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚካሄድ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የፕሮግራሞቹን ቀረጻ ማጠናቀቅና ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ ነው።

ፕሮግራሙ የቀደመውን የልማት ሥራ በማስቀጠል በውጤት ተኮር አተገባበር ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በተለይም በድርቅ ተጋላጭ አካባቢዎች፣ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የንጹህ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም በስደተኞች መጠለያ አካባቢዎች ተደራሽና ዘላቂ የውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎት ለማቅረብ ያለመ ነው።

የሥራ ተልዕኮው ዋና ዋና ዓላማዎች የፕሮግራሙን ቀረጻ ማጠናቀቅ፣ ፕሮግራሙን በገንዘብና በቴክኒክ የሚደግፉ የልማት አጋር ድርጅቶችን መለየት፣ የትግበራ ሰነድ ማዘጋጀት፣ እንዲሁም የፋይናንስ፣ የግዥና የአካባቢ ጥበቃ ጥናቶችን ማጠናከር ናቸው።

በውይይቱ ላይ የመሪ ኮሚቴ አባላት፣ የፕሮግራሙ ተወካዮች፣ ከጤና፣ ከትምህርትና ከገንዘብ ሚኒስቴር የተውጣጡ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዴንማርክ፣ ከኔዘርላንድ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት የተውጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በመክፈቻው ላይ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኜ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የፕሮግራሙ ተልዕኮ ግቡን እንዲመታ ልዩ ትኩረት ይሻል ያሉ ሲሆን ፣ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ የፕሮግራሙን ቀረጻና የትግበራ ሂደት ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።

ፕሮግራሙ በመንግሥትና በልማት አጋር ድርጅቶች መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር፣ የንጹህ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎትን በተለይም ተጋላጭና አገልግሎቱ በበቂ ሁኔታ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ለማስፋፋት የሚያግዝ መሆኑንና ሌሎች አስተያየቶች ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦች ተጠቁመዋል።

Share this Post