ኢትዮጵያ ምርታማነትንና የኃይል ዋስትናን የሚያረጋግጠውን "NEP 3.0" ፕሮግራም ይፋ አደረገች
በአዲስ አበባ በበመካሄድ ላይ በሚገኘው 3ኛው የውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም (NEP 3.0) ይፋ ተደርጓል።
ጥቅምት 17/2019(ው.ኢ.ሚ)
3ኛው የኃይል እና የውሃ ሳምንት (3rd Energy and Water Week) ላይ የውሃ እና ኤነርጂ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ አጋሮች ጋር በመተባበር "ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም 3.0 (NEP 3.0)" በይፋ አስተዋውቋል።
በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኤሌክትሪፊኬሽንና ኢነርጂ መረጃ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ እንደገለጹት፤ አዲሱ NEP 3.0 ፕሮግራም የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ አካሄድ ከመሰረቱ የሚቀይር አዲስ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም የነበረውን "መስመርና ቆጣሪ የመዘርጋት" ትኩረት በመቀየር፣ ኤሌክትሪክን በቀጥታ ከምርታማነት፣ ከኢኮኖሚ እድገት እና ከዜጎች ማህበራዊ ሂወት ጋር ማጣመር ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም NEP 3.0 የኤሌክትሪክ ኃይልን ከግብርና ማቀናበሪያዎች፣ ከፀሐይ ኃይል መስኖ፣ ከእህል ወፍጮዎች፣ ከዶሮ እርባታ፣ ከጨርቃጨርቅ ኢንደስትሪዎች እና ከዲጂታል መዋቅር ጋር በጥብቅ እንደሚያያዝ ገልፀዋል።
አቶ መስፍን በማከል በዚህ ፕሮግራም የሚመነጨው የሀይል መጠን ሳይሆን፣ ተመጣጣኝና አስተማማኝ ኃይል ለአባወራዎች፣ ለአርሶአደሮች ፣ ለትምህርት ቤቶችና ለጤና ተቋማት መድረሱ ነው ብለዋል።
በዚህም የኃይል ብክነትን መቀነስ የስማርት ሜትሪንግ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና የታሪፍ ማሻሻያ በማድረግ የማስተላለፍና ማከፋፈል ብክነትን መቀነስ ፣በመረጃ የተደገፈ እቅድ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስር ብሔራዊ የኢነርጂ መረጃ አስተዳደር መዋቅር መዘርጋት፣ በመንግስት እና በግል ዘርፍ አጋርነት አማካኝነት ከዋናው መስመር ውጭ ያሉ አነስተኛ የፀሐይ ኃይል አውታሮችን (Solar Mini-Grids) ዋና ተግባር መሆኑም ተገልጿል ።
በተጨማሪም በጉባኤው ላይ የውሃ፣ ኢነርጂ፣ ምግብና አየር ንብረት (WEFC) ትስስርን ማጠናከር እንዲሁም የቤት ውስጥ ጢስ ብክለትን የሚቀንሱ ንጹህ የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የእናቶችን ጤና መጠበቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመልክቷል።