የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሠ ምድር ውሃ የአየር ንብረት መቋቋም ፕሮጀክት (Horn of Africa Groundwater for Resilience Project) የ2018 ዓ.ም. የአፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ።

የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሠ ምድር ውሃ የአየር ንብረት መቋቋም ፕሮጀክት (Horn of Africa Groundwater for Resilience Project ) የ2018 ዓ.ም. የአፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ነው።

ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ)

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሠ ምድር ውሃ የአየር ንብረት መቋቋም ፕሮጀክት (Horn of Africa Groundwater for Resilience Project ) የ2018 ዓ.ም. ሲተገበሩ የቆዩ ፕሮጀክቶችን የሚመለከት አጠቃላይ የአፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

በግምገማው ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪዎች፣መካከለኛ አመራሮች፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ ኮንሰልታንቶች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሠ ምድር ውሃ የአየር ንብረት መቋቋም ፕሮጀክት (Horn of Africa Groundwater for Resilience Project ) በዓለም ባንክ የሚደገፍና ክልላዊ መሆኑ የተገለጸ መሆን ይህ የሆነበት ዋና ምክንያትም ከአንድ በላይ አገሮች በጋራ የሚሳተፉበትና የከርሠ ምድር ውሃ ብዙ ጊዜ በክልል ደረጃ ትብብር የሚያስፈልገው በመሆኑና ፕሮጀክቱን በአፍሪካ ቀንድ ያሉ በርካታ አገሮች በጋራ የሚተገብሩት በመሆኑ መሆኑ በመክፈቻው ላይ ተብራተብራርቷል።

መድረኩ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በጥልቀት ለመገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከር፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመለየትና ለቀጣይ ሥራዎች የሚያግዙ የጋራ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

በግምገማው ወቅት በፕሮጀክቶቹ የተመዘገበው አጠቃላይ የፊዚካልና የፋይናንስ አፈጻጸም በዶ/ር ዘበነ ላቀው እና በዶ/ር ከበደ ገርባ በዝርዝር ቀርቧል።

በሪፖርቱም የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፣ የአፈጻጸም ደረጃዎች፣ የበጀት አጠቃቀም፣ የሥራ ፍጥነት እንዲሁም በፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም የታዩ ተግዳሮቶች በስፋት ተዳሰዋል።

በተጨማሪም አማካሪዎችና ተቆጣጣሪዎች በክትትል ሥራቸው የተመለከቷቸውን ጠንካራ አፈጻጸሞች፣ የጥራት ማረጋገጫ ሂደቶች፣ የጊዜ አያያዝ እና መሻሻል የሚፈልጉ ክፍተቶችን በዝርዝር ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።ይህም የፕሮጀክቶቹን ቀጣይ አፈጻጸም ለማሻሻል ተግባራዊ ምክረ ሀሳቦችን ለማመንጨት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

በመድረኩ ላይ ኮንትራክተሮች፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች የራሳቸውን ልምድ፣ አስተያየትና የመፍትሄ ሀሳቦች በማቅረብ የጋራ ውይይት ያካሂዳሉ።

በተለይም የግንባታ ፍጥነትን ማሻሻል፣ የፋይናንስ አስተዳደርን ማጠናከር፣ የግዥ ሂደቶችን ማፋጠን፣ የጥራት ቁጥጥርን ማጠናከር እና በባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅት ማሻሻል ላይ ሰፊ ትኩረት ይሰጣል።

የአፍሪካ ቀንድ ፕሮጀክቶች በከርሰ ምድር ውሃ ፍለጋና ልማት፣ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትን የሚያሳድጉ የሪቻርጅ ሥራዎች፣ የከርሰ ምድር ውሃ ሃብት ጥናትና ማስተር ፕላን ዝግጅት፣ እንዲሁም የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማስፋፋት ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው ለሀገራችን የውሃ ዋስትና ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን፣ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እና በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል ያለውን የቀጠናዊ ትብብር ማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆናቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም የተሳታፊዎች አስተያየትና ምክረ ሀሳቦች ከተሰበሰቡ በኋላ ክቡር ሚኒስትሩ በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮችን በማጠቃለል ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ግልጽ መመሪያ ይሰጣሉ። በዚህም ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ፣ በተፈለገው የጥራት ደረጃ እና በተመደበው በጀት መሠረት እንዲጠናቀቁ አስፈላጊ የክትትልና የድጋፍ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃ

Share this Post