በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ሰኔ 30/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካል ተገኝተው ከምክርቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብ ጥያቄን ለመፍታት እና የሀገሪቱን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ የሚደነቅ ነው፤ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁም ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም ከቀረቡ አስተያየቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አስተያየት ሀገር የማፅናት ልምድ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ለምርጫው ላደረገው አስተዋፅኦ ክብር ይገባዋል ያሉ ሲሆን፤ ሀገራዊ ምክክሩም ለዘመናት የተከማቹ ችግሮችን የሚፈታና አዲስ የጋራ ማህበራዊ ውል የሚፈፀምበት ነው ብለዋል።

ዋጋ እየከፈሉ ሀገር የሚያሻግሩ ተቋማትን አለማመስገን ያለመሰልጠን ምልክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት 10.2 በመቶ በላይ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ተጠናቆ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ቁርጠኝነት ይስፈልጋል፤ የተበጀተውንም በጀት በአግባቡ በመጠቀም ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም አሳስበዋል።

Share this Post