በ3ኛው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት የኢነርጂ ደህንነትንና የተፋጠነ ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ ውይይቶች ተካሄዱ
በ3ኛው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት የኢነርጂ ደህንነትንና የተፋጠነ ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ ውይይቶች ተካሄዱ
አዲስ አበባ — ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም
(ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ሦስተኛው የውኃና ኢነርጂ ሳምንት (ኢነርጂ ቀን) ላይ የሀገሪቱን የኃይል ዋስትና የሚያረጋግጠውና ተደራሽነትን የሚያፋጥነው ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ማቅረቢያ መርሃ-ግብር (NEP 3.0) ላይ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
በዕለቱ “ሁለንተናዊ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን፣ የኢነርጂ ደህንነትን እና ተመጣጣኝ የኢነርጂ ተደራሽነትን ማፋጠን፤ከመስመር መዘርጋት አንስቶ እስከ ውጤታማ አጠቃቀም ድረስ” በሚል ርዕስ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ላይ በአወያዩ አቶ ሳምሶን ቶሎሳ ለቀረቡ ቁልፍ ጥያቄዎች በፓናሊስትነት የተሳተፉት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ የዓለም ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።
አዲሱ NEP 3.0 ስትራቴጂ ከቀደሙት ምዕራፎች የሚለይባቸው መንገዶች፣የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ለማፋጠን መሰራት ያለባቸው ስራዎች፣አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች፣ የዘርፉ የህግ ማዕቀፎችን በማጠናከር በኩል የሚከናወኑ ተግባራት፣የአለም ባንክ ለዘርፍ እየሰጠ ያለው ድጋፍና የልማት ባንክ ውጤታማነት እንዲሁም ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን እንድታስፋፋ የግሉ ሴክተር ሚና በሚሉ የመወያያ ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ በተለያዩ አካላት ከኢነርጂ መረጃ ጋር የተገናኙ ገለጻዎች፣ጥናታዊ ጽሁፎች፣የኢነርጂ ፓሊሲ ክለሳ ማብራሪያዎች እየቀረቡበት ውይይቱ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል።