3ኛው የውሃና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ መዚየም በተለያዩ ሁነቶች እየተካሄደ ነው
ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው 3ኛው የውሃና ኢነርጂ ሳምንት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተለያዩ ሁነቶች እየተካሄደ ነው።
"Advancing Science based Policy and Partnerships for a Water and Energy Secure Future" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የውሃና ኢነርጂ ሳምንት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ውሃን በፍትሃዊነትና በእኩልነት መጠቀም እንዲቻል በቅንጅትና በትብብር የምትሰራ ሲሆን፤ ውሃ ፖለቲካዊ ድንበር የሌለው በመሆኑ በጋራ ተጠቃሚነት እሳቤ ሊመራ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።
የውሃ ሀብትን የተመለከቱ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ውሃን በዘላቂነትና በሳይንሳዊ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችሉ የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ታሳቢ ያደረጉ ፖሊሲዎችና ግብዓቶች የሚሰበሰቡበት መድረክ ሲሆን በቴክኖሎጂ የታገዙ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ፣ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው ፍላጎት ጋር የተመጣጠነ መሠረተ-ልማት መገንባት የሚያስችል ሰፊ የውሃ ሀብት እንዳላትም በመድረኩ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሩፕ እና በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ፓርለስ ካራምባ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከግሉ ዘርፍና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
መድረኩ ላይ በአካል መሳተፍ ያልቻሉ ተሳታፊዎችም በዙም የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውሃውና በኢነርጂው ዘርፍ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለመጋራት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመጠቀም እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል።