የ2030 ዲጂታል ኢኮኖሚ ራዕይን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የe-GP ሥልጠና ተሰጠ

የ2030 ዲጂታል ኢኮኖሚ ራዕይን ወደ ተግባር የሚያሸጋግር የe-GP ሥልጠና ተሰጠ

መስከረም 14/2019 ዓ.ም — ው.ኢ.ሚ.

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራርና ለግዥ ባለሙያዎች በመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት (e-GP) ሥርዓት አጠቃቀም ላይ ሥልጠና ሰጠ።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የሚኒስቴሩ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሼ፣ የe-GP ሥርዓት ከዕለታዊ የግዥ ሂደት በላይ የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂንና የመንግሥት የአሠራር ሪፎርምን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

e-GP የግዥ ሂደቶችን በዲጂታል መንገድ በመመዝገብ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማጠናከር፣ ጊዜና ወጪን ለመቀነስ፣ የአቅራቢዎችን ተሳትፎና ውድድር ለማስፋት እንዲሁም ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለውሳኔ አሰጣጥ ለማቅረብ ያግዛል ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የሥርዓቱ ስኬት በቴክኖሎጂው ዝግጁነት ብቻ ሳይሆን በአመራሩ ቁርጠኝነትና በባለሙያዎች የዲጂታል ክህሎት ደረጃ ላይ እንደሚመሰረት አስገንዝበዋል።

ለሥልጠናው ተሳታፊዎችም የe-GP ሥርዓቱን በተግባር በመጠቀም፣ የግዥ ሂደቶችን በቅልጥፍና በመፈጸምና የዲጂታል አሠራርን በተቋሙ በማስፋፋት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሥልጠናው የሚኒስቴሩን የግዥ አሠራር ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገርና የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ራዕይን በተቋማዊ ደረጃ ወደ ተግባር ለመለወጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የወረቀት ስራን በመቀነስ የግዢ ሂደቱን ፈጣን፣ ግልፅ፣ ተከታታይ እና በቀላሉ ሊመዘገብና ሊከታተል የሚችል ለማድረግ የሚያግዝ እንደሆነም ተጠቁሟል።  

የተቋሙን ተጨማሪ መረጃ ለማገኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikt

 

Share this Post