የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምን ገመገመ ፡፡

ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም. ( ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን በማኔጅመንት ደረጃ ገምግሟል፡፡

በመርሀ ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በፕሮጀክት ደረጃ እና በስራ ክፍል ደረጃ በጥልቀት በመገምግም ለቀጣይ በጀት አመት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ገልጸዋል፡፡

በግምገማ መመደረኩ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዓለሙ መንገሻ የሚኒስቴር መ/ቤቱን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እና በጀት አጠቃቀም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ተይዘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ እና በተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ ዋና ዋና የዘርፎች ተግባራት ክንውን፤ በፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች በየክልሎቹ የታየው አፈጻጸም በንጽጽር በዝርዝር ቀርቦ ተግምግሟል፤ በበጀት ዓመቱ በመደበኛ እና በፕሮጀክቶች የበጀት አጠቃቀም/አፈጻጸም ከ 2017 በጀት አመት አፈጻጸም አንጻር በዝርዝር ቀርቧል፤ ከለጋሽ ድርጅቶች እና ሀገራት ጋር የተደረጉ የአጋርነት ሥራዎች፤ በፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ የመፍትሔ አማራጮች፤በክልሎች በኩል ከተሞች የወሰዷቸው የረጅም ጊዜ ብድር አመላለሶች አሁናዊ ቁመና፤ በመ/ቤቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች (ለሚኒስቴር መ/ቤቱ እና ለክልሎች) የተሰጡ ዘርፈ ብዙ የአቅም ግንባታ ሥራዎች፤ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ከመደበኛ ሥራዎች በዘለለ በተፈጥሮ እና ሰውሰራሽ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተደረጉ ሰብአዊ ድጋፎች እና ሌሎች ክንውኖች በዝርዝር ቀርበዋል።

የቀረበውን መነሻ ሪፖርት በማድረግ ክቡር ሚንስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የማኔጅመነንት አባላቱ ጥያቄዎች እና ገንቢ አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡

Share this Post