የባዘርኔት 2ኛው ብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2019 በጀት ዕቅድ ላይ መከረ።
የባዘርኔት 2ኛው ብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2019 በጀት ዕቅድ ላይ መከረ።
አዲስ አበባ:-ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚተገበረው የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ (BaSRINET) ፕሮጀክት 2ኛው ብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርትና የ2019 በጀት ዕቅድ ላይ መከረ።
ውይይቱን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ እና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ከቢሮ አደረጃጀት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ምደባ ተደርጎ በበጀት አመቱ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበረ አስታውሰዋል።
ክቡር አቶ ሞቱማ አያይዘውም በሁለቱ ቤዚኖች ላይ በቂ ባለሙያ የተመደበ ሲሆን በቀጣይ ከዚህ የበለጠ አፈፃፀም እንዲኖር ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
የጣሊያን መንግስት ተወካይ Mr. Luca Carpintieri በበኩላቸው በቀረው ሪፖርት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም አድንቀው፤ በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ከዚህ የበለጠ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ (BaSRINET) ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዕቅድን እንዲሁም የፕሮጀክት አፈፃፀም መመሪያ ምንነትን በአማካሪው አድማሱ ቴሶ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴ አቅርበው በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።
የባዘርኔት ፕሮጀክት የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር በቤዚኖች ዕውን እንዲሆን ከሚያግዙ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን፤ በአዋሽ እና በዋቢሸበሌ ቤዚን የሚገኙ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን የመቋቋም አቅማቸውን በማጎልበት በውሃ ላይ የተመሰረተ ዘላቂ የኑሮ አማራጮችን መፍጠር ያለመው ነው።
በጣሊያን መንግስት የሚደገፈውና በሁለቱ ቤዚኖች ላይ የሚተገበረው ፕሮጀክት የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር (IWRM) ለማሳለጥ የመረጃ ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የውሃ ተደራሽነትን ማሳደግ፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን እንዲያገግሙ ማድረግ፣ የተቋማትን አቅም ማሳደግ እና የኢነርጂ ተደራሽነትን ማስፋት ላይ ያለመ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የፕሮጀክት አስተዳደር እና ቅንጅት፣ የውሃ ተፋሰስ መረጃ አያያዝ፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የውሃ አቅርቦትና ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የተፋሰስ እና የመከላከያ ቀጠና (Buffer Zone) አስተዳደርን ማሻሻል እና ቴክኒካዊና ተቋማዊ የቁጥጥር አቅምን ማጠናከር ላይ ውጤታማ ስራ መሰራቱን በሪፓርቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ ከግብርና፣ ከገንዘብ እና ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እና ከአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የተውጣጡት ብሔራዊ ስትሪንግ ኮሚቴዎች የተሳተፉ ሲሆን የ2019 በጀት አመት የተግባራት ዕቅድን፣ የፕሮጀክት አፈፃፀም መመሪያን /PIM/ እና ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ በጀትን አፅድቀዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto