በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገነቡ 14 የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ከ370 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የስራ ውል ስምምነቶችን ተፈራረመ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገነቡ 14 የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ከ370 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የስራ ውል ስምምነቶችን ተፈራረመ።

ሰኔ 26/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌ ክልሎች ከከ370 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 14 የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ከአራት ድርጂቶች ጋር ውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በማከል የአፍካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ፕሮጀክት ከተጀመረ 3 አመት የሞላው መሆኑን ገልጸው በአጭር ጊዜ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመፍታ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ዛሬ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በብልዲገሉ እና ሆሞሻ ወረዳዎች 4 የውሃ ጉድጓዶችን ለመቆፈርና ለመገንባት ከጽናት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በ91,429,600.00 ብር ሶማሌ ክልል በኮረሃይ ዞን ዶባወይን ወረዳ እና በዳዋ ዞን ከዳዱማ ወረዳ 3 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን ለመቆፈር ከአል ባዴ ጠቅላላ ኮንስትራክሽንና የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጋር በ59,164,395.00 ብር ድሬ ጠያራ እና ጉባ ቆሪቻ ወረዳዎች እስከ 250 ሜትር ጥልቀት ያላቸውን 3 የውሃ ጉድጓዶች ለመቆፈር ለማያ ሃርድ ሮክ የውሃ ቁፋሮ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከፍተኛው የገንዘብ መጠን የሆነው 122,550,359.50 ብር ሀሰሊሶ እና ጄልዴሳ ወረዳዎች በድምሩ 4 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን እስከ 250 ሜትር ጥልቀት ያላቸውን ለመገንባት ከከስኪ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በ96,908,556.24 ብር ስምምነት መፈረሙን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር (MoWE) ስር የሚመሩ ሲሆን፣ በተለዩት የአገሪቱ አካባቢዎች ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ 370,053,310.74 ብር ውል መፈረሙን በመግለጽ ስራው በ3 ወር ጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቅ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገልጸዋል፡፡

ለማያ ሃርድ ሮክ የውሃ ቁፋሮ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ጸጋዬ ውል የገቡ ድርጂቶችን በመወከል ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉ መሆናቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድመው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡

Share this Post