የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራምና የኢትዮጵያ ዘላቂ የውሃ ፕሮግራም በውጤት ተኮር የፋይናንስ ድጋፍ ለማስፈጸም የተደረገው ውይይት ተጠናቀቀ

የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራምና የኢትዮጵያ ዘላቂ የውሃ ፕሮግራም በውጤት ተኮር የፋይናንስ ድጋፍ ለማስፈጸም የተደረገው ውይይት ተጠናቀቀ

ህዳር 11/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)

የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሦስተኛ ምዕራፍ ፕሮግራም (OWNP-CWA Phase III) እና የኢትዮጵያ ዘላቂ የውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ንጽህና ፕሮግራም (ESWAP) በውጤት ላይ በተመሠረተ የፋይናንስ ድጋፍ (Program-for-Results/PforR) ለማስፈጸም በፕሮግራሞቹ ቀረጻና የትግበራ ዝግጅት ላይ ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

ውይይቱ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማትና የልማት አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ ተወካዮችን በማሳተፍ የተካሄደ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የፕሮግራሞቹን ዝርዝር ቀረጻ ማጠናቀቅ፣ ለትግበራ ዝግጁ ማድረግና የሚያስፈልጉ የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የተቋማዊ ዝግጅቶችን ማጠናከር ነው።

የፕሮግራሞቹ ዋና ትኩረት የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመጸዳጃ ቤት፣ የፍሳሽና የአካባቢ ንጽህና አገልግሎቶችን ማስፋፋትና ጥራታቸውን ማሻሻል ነው። ፕሮግራሞቹ የቀደሙትን የውሃና ሳኒቴሽን ልማት ሥራዎች በማስቀጠል፣ በተጨባጭ ውጤትና በተረጋገጡ የአፈጻጸም ግቦች ላይ በማተኮር የሚተገበሩ ይሆናል ሲሉ የፕሮግራሞቹ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ ገልጸዋል።

በፕሮግራሞቹ መሠረት የውሃና ሳኒቴሽን ልማት ሥራዎች በ103 የገጠር ወረዳዎች፣ ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ 8 አካባቢዎች፣ በ5 መካከለኛ ከተሞች፣ በ15 አነስተኛ ከተሞችና ስደተኞችን በሚያስተናግዱ 22 ወረዳዎች ይከናወናሉ። በእነዚህ አካባቢዎች የንጹህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎቶችን ተደራሽነት፣ ጥራትና ዘላቂነት ለማሻሻል ትኩረት ይሰጣል።

በተጨማሪም በ22 ሁለተኛ ደረጃ ከተሞች የውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎቶችን ለማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ቅልጥፍናና ውጤታማነት ለማሳደግ የተቋማዊ ማሻሻያና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ።

በፕሮግራሞቹ ትግበራ ወቅት ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና ስደተኞችን በሚያስተናግዱ አካባቢዎች ዘላቂና ተደራሽ የውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎት ማቅረብ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል።

በምክክር መድረኩ የፕሮግራሞቹን የትግበራ ሰነዶች ማዘጋጀት፣ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርጉ የልማት አጋር ድርጅቶችን ማሳተፍ፣ የፋይናንስና የግዥ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣ እንዲሁም የአካባቢና ማኅበራዊ ጥበቃ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ የመሪ ኮሚቴ አባላት፣ የፕሮግራሞቹ ተወካዮች፣ ከጤና፣ ከትምህርትና ከገንዘብ ሚኒስቴር የተውጣጡ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዴንማርክ፣ ከኔዘርላንድ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት የተውጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ በመንግሥትና በልማት አጋር ድርጅቶች መካከል ያለውን ትብብርና ቅንጅት ማጠናከር፣ የተቀናጀና ውጤት ተኮር የትግበራ ሥርዓት መዘርጋት፣ በተለይም ተጋላጭና አገልግሎቱ በበቂ ሁኔታ ያልደረሰባቸው አካባቢዎች የንጹህ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ማስፋፋት እንደሚገባ የሚያመለክቱ ሐሳቦችንና ምክረ ሐሳቦችን አቅርበዋል።

በመዝጊያው ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኜ፣ ፕሮግራሞቹ የተቀመጡላቸውን ግቦች በተሳካ ሁኔታ እንዲያሳኩ በትግበራ ሂደቱ ጠንካራ ክትትል፣ ተቀናጅቶ መሥራትና ተገቢውን ትኩረት መስጠት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በአጠቃላይ ውይይቱ የፕሮግራሞቹን ቀረጻና የትግበራ ዝግጅት ለማጠናከር፣ በመንግሥትና በልማት አጋር ድርጅቶች መካከል የጋራ ግንዛቤና ቅንጅት ለመፍጠር

Share this Post