ክቡር ዶ/ር ድንቁ ስዩም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ክቡር ዶ/ር ድንቁ ስዩም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ህዳር 03/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በኢነርጂ ዘርፉ የሥራ አፈጻጸም፣ በፕሮጀክቶች አፈጻጸምና በተቋማቱ ቅንጅታዊ አሠራር ዙሪያ ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ የኢነርጂ ዘርፉን የልማት አቅም ለማሳደግ፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦትንና ተደራሽንትን ለማስፋፋት፣ የአገልግሎት ጥራትና ዘላቂነትን ለማሻሻል የአለም ባንክ የሚያደርገው ድጋፍ እንዲሁም በተቋማቱ መካከል ያለውን ቅንጅት ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

ማንኛውንም ስራ ከመስራታችን በፊት ኢኮሎጂውን ማጥናት ያስፈልጋል ያሉት ክብሩ ሚኒስቴር ዴኤታው ከኮፕ-32 ጋር በተያያዘ የሚሰሩ ስራዎችን በትኩረት ማስኬድ እንደሚግባና ተጠያቂ የሚያደርጉንን ተግባራቶችን እንዴት አድርገን መሰረቱን እናፅናው በሚለው ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

እስካሁን በፕሮጀክቶች ላይ የሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች የግዥ ስርዓቱ ላይ ስለሆነ እንዴት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መዘርጋት ይቻላል በሚል ውይይት የተደ ረገ ሲሆን ብድሮችን ስንስማማ በጥንቃቄ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመው፤ የሁለቱ ተቋማት ቅንጅት ወሳኝ ቢሆንም ትልቅ ኢንቨስትመንት በመሆኑ የፓርላማ ድጋፍም ያስፈልጋል ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የኢነርጂ ዘርፍ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለግብርና ምርታማነትና ለአጠቃላይ ማኅበራዊ ለውጥ ያለውን ወሳኝ ሚና በማንሳት፣ በዘርፉ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ፣ ጥራትና ወጪ እንዲፈፀሙ የተቀናጀ ክትትልና የአፈፃፀም ግምገማ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

በተለይም የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ማሻሻል፣ የሥራ ሂደቶችን በተገቢው መንገድ መከታተል፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በወቅቱ መለየትና መፍትሔ መስጠት ለዘርፉ የልማት ግቦች መሳካት ወሳኝ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ዘርፉን ለማስቀጠል

አማራጮችን መጠቀም፣ የፋይናንስ ምንጮችን ማፈላለግና ተቋማቱ በጋራ የተቀመጡ የሥራ ግቦችን በማሳካት፣ የሀብት አጠቃቀምን በማሻሻልና በውጤት ተኮር የአሰራር ላይ በማተኮር የህዝቡን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በየዘርፋቸው እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን፣ የአፈፃፀም ሁኔታዎችንና የሚገኙ የልማት ዕድሎችን በማቅረብ በቀጣይ በጋራ መስራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ውይይቱ በኢነርጂ ዘርፉ የተቋማትን ቅንጅት በማጠናከር፣ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በማሻሻልና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በማስፋፋት ለሀገራዊ የኢነርጂ ልማት ግቦች መሳካት የሚያግዙ የጋራ የስራ አቅጣጫዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ኦልጅራ እና የሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post