እያንሰራራ ያለው የጥጥና ሌሎች አዝዕርቶች ልማት በአፋር ክልል

እያንሰራራ ያለው የጥጥና ሌሎች አዝዕርቶች ልማት በአፋር ክልል

ጥቅምት/30/2019 ዓ ም (ው.ኢ.ሚ) አሚበራ

በአፋር ክልል በዚህ ዓመት በ20 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በመስኖ የጥጥ ልማት እየተካሄደ ይገኛል። ቀደም ሲል በስፋት ይመረት የነበረው ጥጥ ባለፉት ዓመታት ቢዳከምም፣ በአሁኑ ወቅት እንደገና ወደ ምርት እየተመለሰ ነው።

ልማቱ በአውሲ ረሱ፣ በገቢ ረሱ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች እየተካሄደ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የጥጥ ምርት መሰብሰብ ተጀምሯል።

ከጥጥ ልማት በተጨማሪ የጤፍ፣ የሽንኩርትና የተለያዩ የፍራፍሬ ሰብሎች ልማትም እየተስፋፋ ይገኛል። ይህም የክልሉን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግና የምርት ዓይነቶችን ለማብዛት አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

ለልማቱ መስፋፋት በብሔራዊ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ልዩ ክትትልና ድጋፍ የተከናወኑ የጎርፍ መከላከያ ሥራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዚህም የጎርፍ ስጋቶችን በመቀነስ ሰፊ መሬትን ለግብርና ልማት ምቹ ማድረግ ተችሏል።

በአጠቃላይ የጥጥና የተለያዩ ሰብሎችና የፍራፍሬ ልማት መነቃቃት ለክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለምግብ ዋስትናና ለሕብረተሰቡ የኑሮ መሻሻል ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

«ነጩ ወርቅ» እና የተለያዩ የግብርና ምርቶች በአፋር እንደገና እያንሰራሩ ናቸው።

Share this Post