የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ማሻሻልና የተግባር ክትትልን ማጠናከር ይገባል – ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም
የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ማሻሻልና የተግባር ክትትልን ማጠናከር ይገባል – ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም
ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም ከዘርፉ አመራሮች ጋር የፕሮጀክቶችን የተግባራት፣ የፋይናንስ አፈፃፀምና በስራ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ውይይት አካሄደዋል።
የዘርፉ አመራሮች በተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንና የአፈፃፀም ሂደቶችን በማብራራት በአፈፃፀም ወቅትም ያጋጠሟቸውን ችግሮች አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ያልተጠናቀቁ የክፍያ ሂደቶችን የግዥ ስርዓቱ በሚፈቅደው አግባብ በአፋጣኝ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበው፤ የተግባራት እና የፋይናንስ አፈፃፀም እንዲጣጣም በማድረግ፣ ዝቅተኛ አፈፃፀም በሚታይባቸው ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አፈፃፀማቸውን ማሻሻል እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።
በቀጣይም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በክልሎች የሚከናወኑ ስራዎችን ለማጠናከር፣ ዕቅዶችን ከተግባራዊ ስራዎች ጋር በማጣጣም መከለስ እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
ከግዥ ሂደት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትም ትክክለኛና ግልፅ የቴክኒክ መስፈርቶች (Technical Specifications) በማዘጋጀት የግዥ ሂደቱን ማቀላጠፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በውይይቱ የUNDP፣ ASCENT፣ ADELE እና ELEAP ፕሮጀክት አስተባባሪዎች እንዲሁም የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር እና የኢነርጂ ሀብት ጥናት ስራ አስፈፃሚዎች የስራ ሪፖርታቸውን አቅርበው በፕሮጀክቶች አ