የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የትግበራ ዝግጅት እየተጠናከረ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የትግበራ ዝግጅት እየተጠናከረ ነው።

አዲስ አበባ: ጥቅምት 23/2019ዓ.ም

በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ወደ ትግበራ ለማሸጋገርና በሁሉም የአስተዳደር መዋቅሮች በተቀናጀና ወጥነት ባለው መንገድ ለማስፈጸም ከዘርፉ የሪፎርም አምድ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የሪፎርሙን የትግበራ ሂደት ለማሳለጥ፣ በዝግጅት ምዕራፍ የተዘጋጁ ሰነዶችንና የሥልጠና ማዕቀፎችን በመጠቀም ከላይ እስከ ታችኛው የመንግሥት መዋቅር ድረስ በተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲተገበር የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለመለየት ትኩረት ተሰጥቷል።

የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚና የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዐቢይ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ኦልቀባ ባሼ፣ ባለፈው አንድ ዓመት የሪፎርሙ የዝግጅት ምዕራፍ በርካታ መሠረታዊ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ኦልቀባ ገለጻ፣ በዝግጅት ምዕራፉ የሪፎርሙ ሥራዎች በሦስት ዋና ዋና ምድቦች ተከፍለው የተከናወኑ ሲሆን፣ እነዚህም መሠረታዊ የሪፎርም ተግባራት፣ አስተዳደራዊ የሪፎርም ስራዎች እና የፖሊሲ ዋና ዋና ጉዳዮችን ያካትታሉ።

ሥራዎቹም በዘጠኝ የሪፎርም አምዶች የተደራጁ ሲሆን፣ ለሪፎርሙ ትግበራ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችና የሥልጠና ማዘጋጃዎች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል።

አሁን የተያዘው ቀጣይ ሥራ በዝግጅት ምዕራፍ የተመሠረቱትን የሪፎርም አቅጣጫዎች ወደ ተግባር በመቀየር ውጤታማ ትግበራን ማረጋገጥ መሆኑንም አቶ ኦልቀባ ጠቁመዋል።

ይህም በዝግጅት ወቅት የተሠሩ ሥራዎች በሰነድ ብቻ እንዳይቀሩ፣ በተግባር እንዲተረጎሙና በዘርፉ የሥራ አፈጻጸም ላይ የሚታይ ለውጥ እንዲያመጡ የሚያስችል ነው።

አቶ ኦልቀባ እንዳብራሩት፣ የሪፎርሙን ትግበራ እስከ ታችኛው የመዋቅር እርከን ድረስ በተቀናጀና ወጥነት ባለው መንገድ ለማድረስ በየሪፎርም አምዱ የተዘጋጁ የሥልጠና ሰነዶችን በሚገባ መጠቀም ወሳኝ ነው።

ለዚህም ከየአምዱ ሰብሳቢዎች ጋር ውይይት በማድረግ የሥልጠና ሰነዶቹ እንዴት በተግባር እንደሚውሉ፣ የሪፎርሙ ዓላማና አቅጣጫ በሁሉም የሥራ እርከኖች በተመሳሳይ መንገድ እንዲረዳ እንዴት እንደሚደረግ እንዲሁም የትግበራ ሂደቱ የተቀናጀና ውጤታማ እንዲሆን ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎች ላይ እየተመከረ ነው።

የውይይቱ ዋና ዓላማ የተዘጋጁትን የሪፎርም ሰነዶችና የሥልጠና ማዕቀፎች ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችል የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፣ የትግበራ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና ለሁሉም የመዋቅር እርከኖች ተመሳሳይ የአፈጻጸም መሠረት ማዘጋጀት ነው።

ይህም የሪፎርሙ ተግባራት በተበታተነ መልኩ ከመከናወን ይልቅ በአንድ አቅጣጫ፣ በተቀናጀ አሠራርና በጋራ ኃላፊነት እንዲፈጸሙ ያግዛል።

በአጠቃላይ፣ ከዝግጅት ወደ ትግበራ የሚደረገው ሽግግር የሪፎርሙን ውጤት በተግባር ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

በዚህ ሂደት የሥልጠና ሰነዶችን በተገቢው መንገድ መጠቀም፣ በየአምዱ መካከል ቅንጅትን ማጠናከርና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሁሉም የሥራ እርከኖች ማስፈጸም ለሪፎርሙ ስኬታማነት አስፈላጊ መሠረቶች ናቸው ብለዋል።

በየሪፎርም አምዱ በቀረቡት የሥልጠና ሰነዶች ላይ የተሰጡ አስተያየቶችንና የቀረቡ ግብዓቶችን በጥንቃቄ በመገምገም ለሰነዶቹ መሻሻልና ለትግበራው ውጤታማነት ማዋል አስፈላጊ መሆኑን አቶ ኦልቀባ ባሼ አስገንዝበዋል።

የሚቀርቡ አስተያየቶችና ግብዓቶች የሥልጠና ሰነዶቹን ተግባራዊነት ከማጠናከር ባለፈ፣ የሪፎርሙ ዓላማዎች በሁሉም የመዋቅር እርከኖች በወጥነትና በተቀናጀ መንገድ እንዲተገበሩ የሚያግዙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

Share this Post