የውሃና ኢነርጂ ሳምንት የተማሪዎችን ግንዛቤ አሳድጓል
የውሃና ኢነርጂ ሳምንት የተማሪዎችን ግንዛቤ አሳድጓል
ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በ3ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት የቀረበው ኤግዚቢሽን ውሃንና ኃይልን በቁጠባ ስለመጠቀም የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ ጉልህ ሚና አለው።
የቡርቃ ሰበታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሀቢብ እና ሜሮን ገበየሁ ኤግዚቢሽኑን ከጎበኙ በኋላ ውሃንና ኃይልን በአግባቡና በቁጠባ ስለመጠቀም አዳዲስ ግንዛቤዎችን ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ ከኤግዚቢሽኑ በፊት በውሃና ኃይል ቁጠባ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዳልነበራቸው ጠቅሰው፤ የከርሰ ምድር ውሃ በምን ሂደት እንደሚጣራና ለመጠጥ እንደሚውል፣ ዘመናዊ የኤሌክትሪክና የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ኃይልን፣ ጊዜንና ጉልበትን መቆጠብ እንደሚቻል መረዳታቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የኃይል ቆጣቢ መሳሪያዎችንና ምድጃዎችን ሲገዙ የጥራት ደረጃቸው የተረጋገጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ መረዳታቸውን ገልፀዋል።
ኤግዚቢሽኑ ተማሪዎች ስለ ውሃና ኢነርጂ ሀብቶች ያላቸውን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ ሀብቶቹን በኃላፊነት እንዲጠቀሙና የቁጠባ ባህልን እንዲያዳብሩ ዕድል ይፈጥራል።