የአፍሪካን የውሃ ሀብት ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ትብብርና የቴክኖሎጂ ልውውጥ ወሳኝ ናቸው።

የአፍሪካን የውሃ ሀብት ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ትብብርና የቴክኖሎጂ ልውውጥ ወሳኝ ናቸው። አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 17/2019ዓ.ም የአፍሪካን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለማልማትና ለመጠቀም፣ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በቴክኖሎጂ፣ በእውቀት ልውውጥና በትብብር መፍታት ወሳኝ መሆኑ በሦስተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት በሁለተኛው ቀን “የአፍሪካ የውሃ ተግዳሮቶች በቻይናዊ ፕሮፌሰር እይታ” (The Water Challenges in Africa in the Eyes of a Chinese Professor በሚል በቀረበ ፕረዘንቴሽን ላይ ተመላክቷል።. የአፍሪካ የውሃ ሀብትም ለአህጉሪቱ የልማት ግቦች መሳካትና ለሕዝቦቿ የኑሮ ደረጃ መሻሻል የማይተካ ሚና አለው። ሆኖም የውሃ ሀብት በቦታና በወቅት እኩል አለመሰራጨት፣ የዝናብ መዛባት፣ ድርቅና ጎርፍ፣ የውሃ ማከማቻና ማከፋፈያ መሠረተ ልማቶች እጥረት እንዲሁም የውሃ ብክለት የአህጉሪቱን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም እንደ ተግዳሮት ይጠቀሳሉ። የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መጨመርም የውሃ ፍላጎትን እያሳደጉ ናቸው። ይህም የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ማልማትና መጠቀም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል። በአፍሪካ የውሃ ሀብት ልማትና አጠቃቀም ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች የውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት፣ የውሃ ጥራትና ብክለት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሠረተ ልማት እጥረትና የሀብት አስተዳደር ችግሮች ናቸው። የውሃ አቅርቦትን ለሕዝቡ በተረጋጋና በተመጣጣኝ ወጪ ማዳረስ፣ የመጠጥ ውሃን ከብክለት መጠበቅ፣ የውሃ ብክነትን መቀነስና ያሉትን የውሃ ሀብቶች በብቃት መጠቀም በዘርፉ የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው። በተጨማሪም የውሃ ሀብት ልማትን የሚደግፉ የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የተቋማት አቅሞችን ማጠናከር ያስፈልጋል። በተለይም የውሃ ሀብትን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚረዱ ትክክለኛ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ መተንተንና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መጠቀምም ትልቅ ትኩረት ይሻል። የውሃ ሀብት ልማት ዕድሎችና ከቻይና ሊወሰዱ የሚችሉ ተሞክሮዎች አፍሪካ በውሃ ሀብት ልማት ረገድ ያሉባትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በጋራ ምርምር፣ በሙያተኞች ልምድ ልውውጥና በዘላቂ የልማት አጋርነት ላይ ትልቅ ዕድል አላት። ቻይና በውሃ ሀብት አስተዳደር፣ በውሃ ማከማቻና ማከፋፈያ፣ በመስኖ ልማት፣ በድርቅና በጎርፍ መከላከል እንዲሁም በውሃ ጥራት ጥበቃ ዘርፎች ያካበተችው ልምድ ከአፍሪካ አገራት ጋር ሊጋራ የሚችል የትብብር ዕድል ይፈጥራል። በተለይም ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን ማስተላለፍ፣ የውሃ ሀብት መረጃዎችን ማጋራት፣ የሙያተኞችን አቅም ማጎልበትና በጋራ የምርምር ፕሮግራሞች ላይ መሥራት ለዘላቂ የውሃ ልማት የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ይህንንም ለማሳካት የአፍሪካ አገራት የየራሳቸውን የውሃ ሀብት ሁኔታ፣ የልማት ቅድሚያዎችና የቴክኖሎጂ ፍላጎቶች መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን መተግበር ያስፈልጋል። የአፍሪካና ቻይና ትብብር ለውሃ ዋስትና በውሃ ሀብት ልማት ውስጥ የአገራት ትብብር የልማት አቅምን ከማሳደግ ባለፈ፣ የጋራ የውሃ ሀብቶችን በፍትሐዊነትና በዘላቂነት ለመጠቀም ያስችላል። ይህ በተለይ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የውሃ ተፋሰሶች ባሉባቸው አገራት መካከል የጋራ ዕቅድ፣ የመረጃ ልውውጥና የተቀናጀ አስተዳደር አስፈላጊነትን ያጎላል። የአፍሪካና ቻይና ትብብር በቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት፣ በሰው ኃይል ልማትና በልምድ ልውውጥ ላይ በማተኮር የውሃ ሀብትን ለሕዝብ ጥቅምና ለኢኮኖሚ ልማት የማዋል አቅምን ሊያጠናክር ይችላል። በአጠቃላይ፣ የአፍሪካን የውሃ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ፣ የግሉን ዘርፍና የልማት አጋሮችን ተሳትፎ ማበረታታትና በአገራት መካከል የልምድ ልውውጥን ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል። የሦስተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት የመሰሉ መድረኮችም የውሃና ኢነርጂ ዘርፎችን ተግዳሮቶች ለመወያየት፣ የተለያዩ አገራትን ልምድ ለመጋራትና ለጋራ የልማት መፍትሔዎች መሠረት ለመጣል ጠቃሚ ዕድል ይፈጥራሉ።

Share this Post