ሦስተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት የዘርፎቹን የልማት አቅጣጫ ለመወሰንና የአጋርነት ትብብርን ለማጠናከር ወሳኝ መድረክ ነው

ሦስተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት የዘርፎቹን የልማት አቅጣጫ ለመወሰንና የአጋርነት ትብብርን ለማጠናከር ወሳኝ መድረክ ነው — ዶ/ር ሚካኤል መሃሪ አዲስ አበባ፦ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም ሦስተኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ፣ የቀጣይ ልማት አቅጣጫዎችን ለመወሰንና ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ወሳኝ መድረክ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ሚካኤል መሃሪ ገለጹ። ዶ/ር ሚካኤል እንደገለጹት፣ በ አምስቱ ቀናት በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የተሰሩ ሥራዎች፣ የታቀዱ የልማት ዕቅዶችና የዘርፎቹ ተግዳሮቶች የሚዳሰሱ ሲሆን፣ ሳይንሳዊ ጥናቶች፣ የልምድ ልውውጦችና የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ። የሳምንቱ ዋነኛ ዓላማ የውሃና ኢነርጂ ሀብቶችን ለሀገራዊ ልማት በተቀናጀና በዘላቂነት ለመጠቀም፣ የአጋር አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግና ለቀጣይ ልማት የሚያስፈልጉ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ሀብቶችን ለማሰባሰብ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። በመጀመሪያው ቀን በውሃ ሀብት ጥበቃ፣ በተፋሰስ ልማትና በሥነ-ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ይካሄዳሉ። በተለይም ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ የተፋሰስ ጥበቃና ልማት ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለው ጠቀሜታ፣ የውሃ ሀብት አጠቃቀምና በተፋሰስ ልማት ዙሪያ የጋራ ተሳትፎን ማጠናከር ላይ ጥናቶችና የፓናል ውይይቶች ይቀርባሉ። በሁለተኛው ቀን የኢትዮጵያን የኢነርጂ አቅርቦት ማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነትን ማሳደግና የሀገሪቱን የኢነርጂ ማዕከላዊነት ማጠናከር በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል። በምሁራንና በተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ከካሜሩን፣ ከኬንያና ከአንጎላ ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር በኢነርጂ ልማት ላይ የልምድ ልውውጥና የትብብር ውይይት ይካሄዳል። ሦስተኛው ቀን በውሃ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና ዘላቂ አጠቃቀም ላይ ያተኩራል። ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት ለመጠጥ ውሃ፣ ለመስኖ ልማት፣ ለኢነርጂ ምርትና ለሌሎች የልማት ዘርፎች በተቀናጀ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች ይቀርባሉ። ከውሃ ሀብት ጋር በተያያዙ ዘርፎች የሚሰሩ ተወካዮችም በፓናል ውይይት ይሳተፋሉ። በአራተኛው ቀን ከተለያዩ የልማት አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ (Multi-Stakeholder Forum) ይካሄዳል። መድረኩ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የሚታዩ የልማት ፍላጎቶችን ለመለየት፣ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍን ለማሳደግ፣ የእውቀት ልውውጥን ለማጠናከርና የጋራ የልማት ሥራዎችን ለማስፋፋት ያለውን ሚና ያጠናክራል። በአምስተኛውና የመጨረሻው ቀን በድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት አስተዳደርና ትብብር ላይ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ ዕለት ከድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና ተፋሰሶች ጋር በተያያዙ ጥናታዊ ጽሑፎችና የአሠራር መመሪያዎች ላይ ውይይት ይደረጋል። የጋራ የውሃ ሀብቶችን ለመጠጥ ውሃ፣ ለመስኖ ልማት፣ ለኢነርጂ ምርትና ለሌሎች የልማት ፍላጎቶች በዘላቂነት ለመጠቀም የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎችም ይመከራሉ። በተጨማሪም በተለያዩ ወቅቶች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን የመሩ ሚኒስትሮች በተቋሙ የልማት ጉዞ፣ በተከናወኑ ሥራዎችና በተገኙ ውጤቶች ላይ ያላቸውን ተሞክሮና ልምድ የሚያጋሩበት መድረክ ይኖራል። ዶ/ር ሚካኤል በመጨረሻም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘርፎቹን የልማት ጥረቶች ለማስቀጠልና የተገኙ ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ ለ

Share this Post