ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። አዲስ አበባ : መስከረም 28/2019ዓ.ም በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ያገለገሉት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው ቸሹመዋል። ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባሳለፉት የሥራ ዘመን በኢነርጂ ልማት፣ በኃይል አቅርቦት መስፋፋት፣ በኢነርጂ ተደራሽነት እና በዘርፉ የልማት አቅም ማሳደግ ዙሪያ ከተቋማዊ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። በተለይም የኢነርጂ ዘርፉን ከሀገራዊ የልማት ዕቅዶች ጋር በማስተሳሰር፣ የኢነርጂ ልማትን ለኢኮኖሚያዊ እድገትና ለማህበራዊ ልማት የሚያበረክተውን ሚና ለማጠናከር የተለያዩ የሥራ አቅጣጫዎች እንዲተገበሩ አስተዋፅዖ አድርገዋል። የኢነርጂ ልማት ከመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጋር በተያያዘ የሚኖረውን የልማት ትስስር በማጠናከር፣ በአዲሱ ኃላፊነት በሀገሪቱ የመስኖ ልማት፣ የውሃ አጠቃቀም፣ የቆላማ አካባቢዎች ልማትና የምግብ ዋስትና ዙሪያ የሚከናወኑ ሥራዎችን በማስቀጠል ላይ አዲስ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል። ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በሁለቱም ዘርፎች ያካበቱትን የሙያ እውቀትና የአመራር ልምድ በመጠቀም ለሀገራዊ ልማት የሚኖራቸውን አስተዋፅዖ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩበት ኃላፊነት ሆኖ ቀርቧል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በቀጣይ የሥራ ኃላፊነታቸው ስኬትን ይመኛል። ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetikto

Share this Post