ውሃና ኢነርጂ ለቱሪዝምና ለኢኮኖሚ ዘላቂ ልማት የማይተካ ሚና አላቸው

ውሃና ኢነርጂ ለቱሪዝምና ለኢኮኖሚ ዘላቂ ልማት የማይተካ ሚና አላቸው መስከረም 15/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በኢትዮጵያውያ የመስከረም ወር የአዲስ ዘመን መግቢያ ብቻ ሳይሆን ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ ብዝኃነትን አጉልቶ የሚያሳይና በአደባባይ የሚያንፀባርቁ ልዩ ልዩ በዓላት የሚከበሩበት ወር ነው። እነዚህ በዓላት የህዝቦችን ታሪክና ባህል ከማስተዋወቅ ባሻገር ለቱሪዝምና ለአካባቢያዊ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚፈጥሩት እድል ትልቅ ነው። በዓላት ሲከበሩ የሰዎች እንቅስቃሴ ይጨምራል፤ የጉዞ፣ የመስተንግዶ፣ የምግብ፣ የንግድና የመዝናኛ አገልግሎቶች ፍላጎትም ይጨምራል። ይህ የቱሪዝም እንቅስቃሴ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲካሄድ የተሟላ መሠረተ ልማት ያስፈልጋል። በዚህም ውሃና ኢነርጂ የማይተካ ሚና ይኖራቸዋል። ንፁህና በቂ የመጠጥ ውሃ፣ የንፅህና አገልግሎት መስጫና ተገቢ የውሃ ሀብት አስተዳደር የቱሪዝም መዳረሻዎችን የተሻለ በማድረግ የጎብኚዎችን ልምድ የሚያበረታቱ ናቸው። የውሃ ሀብትን በአግባቡ መጠበቅና መጠቀምም የተፈጥሮ ሀብቶችን ለቀጣይ ትውልድ ከማሻገርም በላይ የውሃ አካላት የቱሪዝም አቅምን ለማሳደግ ያግዛል። ኢነርጂ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ዘመናዊ የቱሪዝም አገልግሎት ከኢነርጂ ተደራሽነት ውጪ ሊታሰብ አይችልም። ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ የባህል ማዕከላትና ሌሎች የቱሪዝም ተቋማት የተረጋጋ፣ ዘላቂና በቂ የኢነርጂ ተደራሽነትና አቅርቦት ይፈልጋሉ። በተለይም የታዳሽ ኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም ከዋናው የኃይል መስመር ርቀው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በቂ ኢነርጂ በማቅረብ የቱሪዝም አቅማቸውን ለማሳደግ ያግዛል፡፡ የፀሐይ፣ የውሃና ሌሎች ታዳሽ የኢነርጂ ምንጮች በዚህ ረገድ ወሳኝነት አላቸው። የውሃና ኢነርጂ ልማት ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ሲነፃፀር አገልግሎቱ ሲሻሻል የቱሪዝም ተቋማት አቅማቸውን ያሳድጋሉ፤ የአካባቢው ንግድ ይንቀሳቀሳል፤ የስራ ዕድል ይፈጠራል። በዚህ ሂደት ከትልልቅ ኢንቨስትመንቶች እስከ አነስተኛ የንግድና የእጅ ስራ ተግባራት ድረስ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በዓላትን፣ ባህልንና ቱሪዝምን ከውሃና ኢነርጂ ልማት ጋር ማስተሳሰር በሀገራዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚፈጥረውን ዕድል የበለጠ በማስፋት ለህይወት መሠረታዊ ፍላጎቶች ብቻ ሳይሆኑ ለቱሪዝም፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለስራ ዕድልና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት አቅም ይፈጥራሉ። የተቋሙን ተጨማሪ መረጃ ለማገኘት ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/ ቴሌግራም http://t.me/mowieethiopia ዌብሳይት http://mowe.gov.et X/ትዊተር https://x.com/mowe_ethiopia ዩቱዩብ https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s ቲክቶክ tiktok.com/@mowetik

Share this Post