የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ!
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 15/2019ዓ.ም.
ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የልማት አቅም ለሀገራዊ ዕድገት፣ ለቀጠናዊ ትስስርና ለጋራ ብልጽግና ለማዋል የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዋን በማጠናከር ላይ ትገኛለች።
በሁለትዮሽና በብዝሃ ወገን ዲፕሎማሲ ከተለያዩ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን የትብብር ግንኙነት በማስፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችንና የልማት አጋርነትን ለማጠናከር እየሠራች ነው።
በተለይም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶችን በፍትሐዊነትና በጋራ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዓባይ ወንዝን ጨምሮ የውሃ ሀብቶችን ለጋራ ልማት ማስተባበር፣ የኃይል ትስስርን ማስፋትና የክልላዊ የኃይል ትብብርን ማጠናከር የዲፕሎማሲያዊ ጥረቷ ዋነኛ አቅጣጫዎች ናቸው።
ይህም የውሃና ኢነርጂ ሀብቶችን በዘላቂነት ለማልማት፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማሳደግ፣ የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅና ለክልላዊ ሰላምና ብልጽግና የሚያግዝ የትብብር መሠረት ይፈጥራል።
ዲፕሎማሲ ለጋራ ጥቅም፤ ውሃና ኢነርጂ ለዘላቂ ልማትና ለጋራ ብልጽግና!
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto