የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም የጋራ ግምገማ ተካሄደ

የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም የጋራ ግምገማ ተካሄደ

መስከረም 4/2019 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) — በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራም (One WASH National Program) የማስጀመሪያ የጋራ ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

በጋራ ግምገማው ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ተገኝተው የፕሮግራሙን አፈጻጸም፣ ያስመዘገበውን እድገት እና በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አስመልክተው ንግግር አድርገዋል።

አምባሳደር ዶ/ር አስፋው በንግግራቸው፣ ፕሮግራሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻልና የተሻለ አፈጻጸም እያሳየ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም ከአጋር ድርጅቶች ጋር የተጠናከረ ቅንጅትና ትብብር በመኖሩ የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክተዋል።

በመድረኩ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ የፕሮግራሙን አፈጻጸም በዝርዝር አቅርበዋል። በተጨማሪም ፕሮግራሙ በቀጣይ የሚያተኩርባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች አብራርተዋል።

የጋራ ግምገማው በፕሮግራሙ አፈጻጸም የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በጋራ በመወያየት የፕሮግራሙን አፈጻጸም የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ከጤናና ትምህርት ሚኒስቴሮች የተውጣጡ የፕሮግራሙ አስፈጻሚዎች ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም በፕሮግራሙ አፈጻጸም፣ በተገኙ ውጤቶች፣ በተግዳሮቶች እና በቀጣይ የሚያስፈልጉ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ጠቃሚ ሀሳቦችና አስተያየቶችን አቅርበዋል።

የጋራ ግምገማው በተለያዩ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅትና ትብብር በማጠናከር፣ የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም እና ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ በመፍታት የብሔራዊ አንድ ቋት ፕሮግራምን የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ለማድረግ ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikt

Share this Post