የማንሰራራት ቀን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሀገራዊ የህዳሴ እና የተስፋ ጉዞ
ጳጉሜ 2/2018ዓም(ው.ኢ.ሚ)
የማንሰራራት ቀን ኢትዮጵያ የነበራትን ታላቅነት በመመለስ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቿን በሙሉ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል የምታደርገውን ሀገራዊ የትግልና የመልሶ ማቋቋም ጉዞ የሚያሳይ ታሪካዊ ምልክት ነው።
በዚህ የዕድገትና የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ደግሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሀገሪቱን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት በመጣል ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ኢትዮጵያ «የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ» በመባል ብትታወቅም፣ ሀብቷን አውጥቶ ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ለዘመናት የነበሩትን ተግዳሮቶ በመስበር ላይ ትገኛለች።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅና ስራ መጀመር፣ የበርካታ ታዳሽ ኢነርጂ ፕሮጀክቶች (የፀሐይ፣ የነፋስና የጂኦተርማል) መስፋፋት እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃን ለሁሉም ዜጎች ተዳራሽ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የማንሰራራት ቀናችን እውን እየሆነ መምጣቱን ማረጋገጫዎች ናቸው።
የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የማንሰራራታችን ዋና ማዕከል የሆነበት ምክንያቶች
በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በማቅረብ ሀገራዊ ምርታማነትን ማሳደግ።
በኃይል ሽያጭ የጎረቤት ሀገራትን የኤሌክትሪክ ፍላጎት በማሟላት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጠናከር።
ንጹህ የመጠጥ ውሃንና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለገጠሩና ለከተማው ህብረተሰብ በማድረስ የወጣቶችና የሴቶችን እንግልት መቀነስ።
በመሆኑም የማንሰራራት ቀን የውሃና ኢነርጂ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠበቅ፣ በማልማትና በመጠቀም ኢትዮጵያን በራሷ እግር የቆመችና የበለፀገች ሀገር ለማድረግ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ታላቅ ቀን ነው።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto