ጥራት ያለው መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ማንሠራራት

ጥራት ያለው መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ማንሠራራት

ጅግጅጋ:- ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሌሎች የሴክተር መሥሪያ ቤቶች ጋር በመሆን በጅጅጋ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ሥራዎችንና የሸበሌ ሪዞርትን ጎበኙ።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማትና የቱሪዝም ልማቶች የሀገሪቱን የማንሠራራት ጉዞ በተጨባጭ እያሳዩ መሆናቸውን ለማስገንዘብ መሆኑ ተገልጿል።

የጅጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ምቾትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ የሚያግዝ ዘመናዊ የከተማ ልማት አቅጣጫ ነው። የተሻለ የእግረኛ መንገድ፣ የአረንጓዴ ልማት ስፍራና ሌሎች የከተማ መሠረተ ልማቶች በተቀናጀ መልኩ መልማታቸው ጅጅጋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎቿ የተሻለች ከተማ ለማድረግ ያለውን አቅም ያሳያል።

የሸበሌ ሪዞርትም በተፈጥሮ ሀብትና በቱሪዝም እምቅ አቅም የተሞላውን የሶማሌ ክልል ሀብት ወደ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድል የመቀየር ሂደት ማሳያ ነው። የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋት የአካባቢውን ተፈጥሯዊ ሀብት ከመጠቀም ባለፈ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለአካባቢያዊ ንግድ መስፋፋትና ለከተማዋ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አዲስ አቅም ይፈጥራል።

በተለይም የውሃ፣ የኢነርጂ፣ የመንገድ፣ የከተማ ልማትና የቱሪዝም መሠረተ ልማቶች በተናጠል ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ሲለሙ የልማት ውጤቱ የበለጠ ዘላቂና ተጨባጭ ይሆናል። ይህም የተለያዩ ተቋማት በጋራ በመሥራት የሀገራዊ ልማት ግቦችን ለማሳካት እያሳዩ ያሉትን ቅንጅታዊ አሠራር ያሳያል።

ጥራት ያለው መሠረተ ልማት የአንድ ከተማ ውበት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እድገት፣ የሥራ ዕድል፣ የኢንቨስትመንት መስፋፋትና የዜጎች የኑሮ ጥራት መሠረት በመሆኑ በጅጅጋ የሚታዩት የኮሪደር ልማትና የሸበሌ ሪዞርት የማንሠራራት ጉዞው በተግባር የሚገለጽባቸው የልማት ፍሬዎች ናቸው።

የሀገር ማንሠራራት በአንድ ዘርፍ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን በውሃና ኢነርጂ፣ በከተማ ልማት፣ በመንገድ፣ በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች የሚፈጠሩ ውጤቶች ሲተሳሰሩ የሚገኝ ሀገራዊ ውጤት ነው።

ከተግዳሮት ወደ ውጤት፣ ከውጤት ወደ ተስፋ፤ ጥራት ያለው መሠረተ ልማት ለኢትዮጵያ ማንሰራራት

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post