የቤዚን ፕላን ክለሳ ሂደት የዴስክ ስተዲ ስራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግምገማ ተጀመረ
የቤዚን ፕላን ክለሳ ሂደት የዴስክ ስተዲ ስራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግምገማ ተጀመረ
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም | ሀዋሳ
የቤዚን ፕላን ክለሳ ሂደት አካል የሆነው የዴስክ ስተዲ (Desk Study) ስራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግምገማ በሀዋሳ ሮሪ ሆቴል መካሄድ ጀመረ።
የግምገማ መድረኩ ዋና ዓላማ በዴስክ ስተዲ ሂደት የተከናወኑ ስራዎችን፣ የተገኙ ግኝቶችንና የታዩ ክፍተቶችን በጋራ በመገምገም ለቀጣይ የቤዚን ፕላን ክለሳ ስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።
በመድረኩ ላይ የስ/ሸ/ሀ/ቤ/አስ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ወንድሙ ታዲዮስ እንደገለጹት፣ የቤዚን ፕላን ለመከለስ የዴስክ ስተዲ ስራው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ የተለያዩ ሙያዎችንና የትምህርት ደረጃዎችን ያካተቱ ባለሙያዎች በጋራ በመስራታቸው ልዩ ልዩ ልምድና እውቀት ለመለዋወጥ እንዳስቻለ ገልጸዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር አስተባባሪ እና የብራይት ፕሮጀክት የቤዚን ፕላን አስተባባሪ ዶ/ር ብዙነህ አሰፋው በበኩላቸው፣ የቤዚን ፕላን ክለሳ ስራው ከኦዲት በተገኘ ግብዓት መጀመሩ ለስራው መሳለጥና ውጤታማነት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።
በክለሳ ሂደቱም ሁሉም የትኩረት መስኮች በጥልቀት እንዲታዩ፣ ክፍተቶች እንዲለዩና ገንቢ ግብዓቶች ተሰብስበው ወደ ቀጣይ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ሂደት እንደሚከናወን አስረድተዋል።
በዕለቱም የጽ/ቤቱ የቤዚን ፕላን ዴስክ ኃላፊ አቶ አበበ አሰሌ በአርባምንጭ ቆይታ የተከናወኑ ስራዎችን በማጠቃለል ለመድረኩ አቅርበዋል።
በመቀጠልም እያንዳንዱ የትኩረት መስክ በቆይታው ያከናወናቸውን ስራዎች በHarmonization Table (የተገኙ ግኝቶችን የማጣጣሚያ ሰንጠረዥ)፣ Gap Matrix (ክፍተቶችን የሚያሳይ ሰንጠረዥ)፣ Review Matrix (የግምገማ ሰንጠረዥ) እና Action Plan for Next Duties (የቀጣይ ስራ ዕቅድ) በመጠቀም ለግምገማ እያቀረበ ይገኛል።
በግምገማው መድረክ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቤዚን ፕላን ዴስክ ኃላፊና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ከውሃና መሬት ልማት ማዕከል ባለሙያዎች፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራማሪዎች እንዲሁም ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከኦሮሚያና ከሲዳማ ክልሎች የውሃ፣ የግብርና፣ የመስኖና የአካባቢ ጥበቃ ቢሮዎች ተወካዮች ተሳትፈዋል። የቤዚን ጽ/ቤቱ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በመድረኩ ተገኝተዋል።
የግምገማ መድረኩ የተዘጋጀው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የውሃና መሬት ሀብት ማዕከል እና የብራይት ፕሮጀክት ባላቸው ትስስርና በተደረገ የበጀት ድጋፍ ሲሆን፣ መድረኩ ለቀጣይ ሁለት ቀናት ይቆያል።
የዴስክ ስተዲ ስራው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግምገማ በተሳታፊ አካላት የሚቀርቡ ግብዓቶችን በማካተት ለቀጣዩ የቤዚን ፕላን ክለሳ ስራ ጠንካራ መሠረት እንደሚፈጥር ይጠበቃል።