በባዘርኔት ፕሮጀክት የአዋሽ ቤዚን ስትሪንግ ኮሚቴ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
በባዘርኔት ፕሮጀክት የአዋሽ ቤዚን ስትሪንግ ኮሚቴ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ ከሚተገብሩ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው በባዘርኔት ፕሮጀክት /BaSRINET/ የአዋሽ ቤዚን ስትሪንግ ኮሚቴ አመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
የግምገማውን መድረክ ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ እና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ስትሪንግ ኮሚቴው በየጊዜው ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ የሚገመግም በመሆኑ በመካከለኛውና በታችኛው አዋሽ ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።
ክቡር አቶ ሞቱማ አክለውም ፕሮጀክቱ ሊጠናቀቅ በቀረው አንድ አመት ቀሪ ስራዎች ላይ በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ጠቁመው፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተነሱ ተግዳሮቶችን በመፍታት በውይይቱ የቀረቡ አስተያየቶችን እንደግብአት መጠቀም ይገባልም ብለዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ በበኩላቸው በተጠናቀቀው በጀት አመት ጥሩ አፈፃፀም መኖሩን ጠቁመው፤ በቀጣይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ዕውን ለማድረግ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ቅንጅት ሊኖር ይገባል ብለዋል።
በአዋሽ ቤዚን በተጠናቀቀው በጀት አመት የተፋሰስ እንክብካቤ ስራዎች (watershed managment) ተግባራዊ ለማድረግ በማህበራት የተደራጁ ወጣቶች ለአካባቢው የሚመጥን ቴክኖሎጂን መሬት ላይ በማውረድ የጎርፍ ሰራዎች፣ አነስተኛ መስኖ እና የፕሮጀክት ጥናት ስራዎች በመጀመራቸው የውሃ ሀብት አስተዳደር ስራዎች በስፋት እየተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል።
የፕሮጀክቱ አመታዊ የተግባራት አፈፃፀም እና የቀጣይ አመት ዕቅድ አተገባበር በአቶ ዮሀንስ ዘሪሁን ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ በቀረቡት ሰነዶች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ በአዋሽ ቤዚን የአፋር ክልል ውሃ ቢሮ ኃላፊዎች፣ አለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) እና በቤዚኑ የባዘርኔት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto