የዋቢ ሸበሌ ቤዚን ባዘርኔት ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴዎች የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ሲገመግሙ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገለጹ።

የዋቢ ሸበሌ ቤዚን ባዘርኔት ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴዎች የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ሲገመግሙ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገለጹ።

ድሬደዋ ነሐሴ12/2018ዓም(ው.ኢ.ሚ)

በምክክር መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ በጣሊያን መንግሥት የሚደገፈው የባዘርኔት (BaSRINET) ፕሮግራም ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በክልሎች የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አውስተዋል።

አቶ ማሙሻ አያይዘውም የዋቢሸበሌ ቤዚን አስተዳደር ሥራዎች ከግብርና፣ መስኖና አካባቢ ጥበቃ ሴክተሮች ጋር በተቀናጀ መልኩ ካልተሠሩ የሚፈለገው ውጤት ሊመጣ እንደማይችል ጠቁመው፣ ይህ ቅንጅት በሀገራችን በኤልኒኖ ምክንያት ሊጎዱ የሚችሉ አካባቢዎችን ለመታደግና የተመደበውን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።

​በሌላ በኩል የብሔራዊ ባዘርኔት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ በበኩላቸው፣ ስብሰባው የፕሮጀክቱን የትግበራ ዝግጅት ለመገምገም፣ የሥራ ድርሻዎችን ለማብራራትና ለቀጣይ ፈጣን ትግበራ ውሳኔዎች ላይ ለመድረስ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሞላ አክለውም ​ስትራቴጂካዊ መመሪያ የመሪ ኮሚቴው ግልጽ መመሪያ እንዲሰጥና የቴክኒክ ኮሚቴው ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ፤​ተጠያቂነትና ግልጽነት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከተስማማንባቸው ውጤቶች ጋር ተያይዞ የኅብረተሰቡን የመቋቋም አቅም እንዲያሻሽል፤​ቅንጅት በብሔራዊና በክልል ደረጃዎች መካከል ቅርብ ግንኙነት እንዲኖር አሳስበው ለተሳታፊዎችና አጋሮች ምስጋና አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይም የስራ አፈፃፀም ሪፓርት እና የ2019በጀት አመት እቅድን በዋቢሸበሌ ቤዚን የባዘርኔት አስተባባሪ አቶ ኤሊያስ ሁሴን ባቀረቡበት ወቅት የተቀናጀ የዉሀ ሀብት አስተዳደር ጥናት በቀላፎ የተጀመረ መሆኑንና

የመጠጥ ዉሀ ጎርፍና አነስተኛ መስኖ ጥናት መጀመሩን በዋናነት ገልጸዋል ።

በቀረበው ሪፓርትና እቅድ ላይ በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ከመድረክ በመስጠት ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post