የተፋሰስ ዕቅድ ክለሳ ሥራ ሂደት ተገመገመ

የተፋሰስ ዕቅድ ክለሳ ሥራ ሂደት ተገመገመ

ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም | አርባ ምንጭ ቀደም ሲል የተዘጋጀውን የ15 ዓመት የቤዚን ፕላን ከአሁኑ ነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም እየተካሄደ ያለው የተፋሰስ ዕቅድ ክለሳ ሥራ ሂደት ተገመገመ።

የክለሳ ሥራው በአምስት የትኩረት መስኮች፤ የውሃ ሥርዓትና አየር ንብረት፣ ባዮፊዚካል፣ የውሃ አጠቃቀምና መሠረተ ልማት፣ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊና የጋራ ጉዳዮች፣ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ሥርዓቶች ተከፋፍሎ እየተከናወነ ይገኛል።

በመድረኩ በሁሉም የትኩረት መስኮች የተሰሩ ሥራዎች፣ የመረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀትና ትንተና ሂደቶች በስፋት ተወያይተው የቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ የክለሳ ሥራው በዘመናዊና ሳይንሳዊ አሠራር እንዲመራና ዓለም አቀፍ መልካም ተሞክሮዎች እንዲካተቱበት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ሥራው በቀጣይ ቀናት የዴስክ ስታዲ (Desk Study) በማካሄድ የሚቀጥል ሲሆን፣ ዓላማውም ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመና ለዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት የሚያግዝ የተሻሻለ የተፋሰስ ዕቅድ ማዘጋጀት ነው። ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post