የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደራዊ ሪፎርም አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፓርት በሲቪል ሰርቪስ ሱፐር ቪዥን ቡድን ቀረበ

የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደራዊ ሪፎርም አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፓርት በሲቪል ሰርቪስ ሱፐር ቪዥን ቡድን ቀረበ

ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቡድን ቀርቧል። በአቀራረቡም በሪፓርት የቀረቡ የሪፎርም ሥራዎችን በቦታው ተገኝተው በማረጋገጥ ቡድኑ በያዘው ቼክ ሊስት መሠረት ግብረመልስ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የብቃት ሥራ አመራር ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አጥሬ እንደገለፁት ስራው በሚኒስቴሩም ሆነ በተጠሪ ተቋማት በቼክ ሊስቱ መሠረት ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ እና በከፍተኛ አመራሩ በጥብቅ ዲስፕሊን የተመራ መሆኑን ማየት ችለናል ብለዋል። አክለውም በእያንዳንዱ አምድ እስከ ተጠሪ ተቋማት የተናበበ ስራ መስራቱን ለማየት ችለናል በማለት ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ ክቡር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወጥ አድርግው ስለመሩ ለሪፎርሙ ከፍተኛ ትኩረት ስለሠጡ በቡድኔና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ስም አመሰግናለሁ ሲሉ ምስጋናቸውን ችረዋል።

በተጨማሪም አቶ ተስፋዬ በማብራሪቸው ይህ የተጀመረው ወጥነት ባለው አደረጃጀት እየተመራ ያለ አሰራር በዚህ ግለት እስከ ትግበራና ማፅናት ምዕራፍ ሊሄድ ይገባል ብለዋል። ሌሎች የሱፐር ቪዥን ቡድን አባላት በግብረ መልስ መድረኩ እንደገለፁት ዘርፏ ለሪፎርሙ የሠጠውን ከፍተኛ ትኩረት እውቅና ሠተው በተለይ በቴክኖሎጂ ስራዎች ከንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር በቴክኖሎጂ ታግዘው የተሠሩ ስራዎች እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚወሠድበት ነው ብለዋል ። አክለውም ቡድኑ ዘርፏ ሳይዘናጋ ቀሪ ስራዎችን ትኩረት ሠቶ በመስራት የዘርፏን ሠራተኞች በተደጋጋሚ በማስገንዘብ የተሻለ ውጤማ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሐብታሙ ኢተፋ ቡድኑ እኛ ለመደገፍ ጎዶሎችንን በማሳየት ማሻሻያ እንድናደርግ ስላደረገው መልካም ነገር አመስግናለሁ በማለት ሪፎርሙን በባለቤትነት ከላይ እስከ ታች በአደረጃጀት የተመራ መሆኑን አፅንኦት ሠተው ገልፀዋል ። ቀጣይም ከፍተኛ አመራሩ እስከ ዘርፍ ድረስ ሪፎርሙን እስከ ትግበራ ምዕራፍ በጥብቅ ዲስፕሊን እንደሚመራ ለቡድኑ አረጋግጠው ክልሎችም ግንዛቤ እንዲኖራቸው የዘርፏ ሪፎርም ስራን በተለያዩ ማድረኮች የማስገንዘብ ስራም እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post