የመረጃ ስርአትን ማዘመን ስራን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፈጸም እንደሚጠቅም ተገለጸ።

የመረጃ ስርአትን ማዘመን ስራን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፈጸም እንደሚጠቅም ተገለጸ።

ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) በተፋሰስ ለሚገኙ የመረጃ ሰበሰቢዎች የተግባርና የንድፈ-ሀሳብ ስልጠና ላይ የመረጃ ስርአትን ማዘመንስራን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፈጸም እንደሚጠቅም ተገለጸ።

​በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት የቤዚን ሀይድሮሎጂ ኢንፎሮሜሽን የግል አማካሪ ዶ/ር ሄርጶ ጉደታ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ለመተግበር ከቀረፃቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ባዘርኔት መህኑን ገልጸው ፕሮጀክቱ ከሚተገብራቸው ተግባሮች የሀይድሮሎጂ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ቀዳሚው መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የሀይድሮሎጂ መረጃ ለመሠብሰብ ስራው ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ማሰልጠንና አቅማቸውን ማሳደግ አስፈላጊ ሲሆን የሀይድሮሎጂ ዳታ ለግድብ፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ እና ለጎርፍ መከላከል ድርቅን ጨምሮ ትክክለኛ መረጃ እንዲሰበስቡ እና እንዲልኩ ታሳቢ በማድረግ ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል።

ደ/ር ሄርጶ በማከል ስልጠናው በዋናነት ​የሀይድሮሎጂ መሠረታዊ እውቀቶች፣ ​የውሃ መጠንና የዝናብ አነባበብ ዘዴዎች ​የመረጃ ምዝገባ፣ ጥራት ቁጥጥርና ሪፖርት አቀራረብ፣​ የመለኪያ መሳሪያዎችና እንክብካቤ ላይ ያተኮረ ሲሆን ሰልጣኞች በሞጆ አካባቢ በሚገኘው የሀይድሮሎጂ ጣቢያ በመጎብኘት የመስክ የተግባር ስልጠናም እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከዶዶላ ጎራ ወንዝ የመጡት የመረጃ ሰብሳቢ ባለሙያ ወ/ሮ ወይንሸት ክብረት በስራ ለይ ያለች መሆኗን ገልጻ ስልጠናው እራሷንና ስራዋን ለማሻሻልና ለማዘመን እንደሚጠቅማት በመግለጽ ስራዋን በስኬት ለማስኬድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊየደርግላቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሌላኛው የዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ የአርሲ ጤች አቅራቢያ የሀረርጌ ወንዝ የሀይድሮሎጂ መረጃ ሰብሳቢ ባለሙያ አቶ ተክሉ ከተማ ስራውን ከጀመሩ ረጅም ጊዜ እንደሆናቸው በመግለድ መረጃ በቀን ሁለት ጊዜ እንደሚሰበስቡና በአግባቡ መረጃ እንደሚልኩ ገልጸዋል።

አቶ ተክሉ ስልጠናው አስፈላጊና ስራውን ለማዘመን ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መስራያ ቤቱ ለስራው አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ቢያደርግ የተሻለ ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል።

​ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com

Share this Post