በብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የኃይል አቅርቦትን በዘላቂነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

በብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የኃይል አቅርቦትን በዘላቂነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ሐምሌ 13/2018 ዓም ውኢሚ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች፣ ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ የADELE ፕሮጀክት ተወካዮች ጋር ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የኃይል አቅርቦትን በዘላቂነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የውይይት መድረኩን በመሩበት ወቅት በብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የኃይል አቅርቦትን በዘላቂነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ከሶላርጋ ተያይዞ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋዎችን በመጠቀም የኃይል ተደራሽነት ችግሮችን መፍታት ይቻላል፤ በቀጣይም የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

የባዮጋዝ ቴክኖሎጂን በተመለከተ ዘርፈብዙ የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ በመሆኑ የሚሰጠውምና የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን ገልፀው፤ በየደረጃው ላሉ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግንዛቤ በማስጨበጥና ተግባራዊ በማደረግ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል።

በመድረኩም ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተው የሚመለከታቸው የክልሉ የስራ ኃላፊዎችም ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የውሃና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ኩመራ በመድረኩ ላይ የተነሳውን ሀሳብ እንደግብዓት በመጠቀም በቀጣይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ለኢነርጂ ዘርፉ ትኩረት እንደሚሰጥም አሳስበዋል።

Share this Post