የገጠርና በጣም ገጠራማ ቦታዎችን በፍትሃዊነት የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሎች ድርሻ የላቀ ነው።

የገጠርና በጣም ገጠራማ ቦታዎችን በፍትሃዊነት የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሎች ድርሻ የላቀ ነው።

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ

አሶሳ፣ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም (Access to Distributed Electricity and Lighting in Ethiopia) ትግበራ፣ መመሪያና በአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ስርዓት ዙሪያ ከቤኒሻንጉል ክልል፣ ዞኖች እና ወረዳዎች ከተውጣጡ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከዞንና ከወረዳ የአደሌ ፕሮጀክት ተወካዮች እና የሶላር አከፋፋዮች ጋር በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ገጠርማ እና በጣም ገጠራማ ቦታዎችን በፍትሃዊነት የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሎች ድርሻ የላቀ ነው ብለዋል።

በተቋሙ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱ ለሆነው ገጠራማ እና በጣም ገጠራማ አካባቢዎችን በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ /Result Based Finance Grant/ የቤተሰብ ሶላር ሆም ሲስተም/Solar Home System/ በገጠር ላሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ለማሰራጨት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል።

የገጠርና በጣም ገጠራማ ቦታዎችን በፍትሃዊነት የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሎች ድርሻ የላቀ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው የብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በምን ደረጃ ላይ እንዳለም ለመገምገም የሚያስችል መድረክ በመሆኑ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራምን ዕውን ለማድረግ ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የአማራጭ ኢነርጂ ልማትን ለማጠናከር ትኩረት መስጠቱን የገለፁት የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ኩመራ ዘርፉን በተቋም ደረጃ በማደራጀት እስካሁን የተሻሻሉ የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ህብረተሰቡ እንዲላመድ በማድረግ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙበት ግንዛቤ በመፍጠር እና የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢን በማምረት ስራ ላይ የተደራጁ ማህበራትን በመደገፍ ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ ባሻገር ሴቶች በማገዶ እንጨት ሰበራ ላይ የሚያባክኑትን ጉልበትና ጊዜን በመቀነስ የሚደርሰውን የአየር ብክለትን መቀነስ ስራ ጥሩ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም አቶ ታሪኩ አክለዋል፡፡

አቶ ታሪኩ አያይዘውም የተጀመረው የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራን አጠናክሮ ተግባራዊ ለማድረግ ከወትሮው በተሻለው ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ በቀለ አምበሳን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች የተሳተፉ ሲሆን በክልሉ የሶላር አቅራቢዎችም ምርቶቻቸውን አስተዋውቀው፤ በሚቀርቡ ፅሁፎች ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ውይይት ይካሄዳል።

Share this Post