የሀዋሳ ሀይቅን ደህንነት ለመጠበቅ የጋራ የባለድርሻ አካላት የስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት እየተካሄደ ነው።
የሀዋሳ ሀይቅን ደህንነት ለመጠበቅ የጋራ የባለድርሻ አካላት የስትሪንግ ኮሚቴ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ሀምሌ 7/2018 ዓ.ም ሀዋሳ,
የሀዋሳ ሀይቅን ደህንነት ለመጠበቅ የጋራ የባለድርሻ አካላት የስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ሀይቁ ካለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስተጋብር አንጻር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራና በተናበበ መንገድ ለሀይቁ ዘላቂ ጠቀሜታ መስራት እንደሚገባ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ/ተወካይ ዶ/ር ወንድሙ ታዲዎስ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣቹ ባሉበት ወቅት ገልጸዋል።
የውሃን ደህንነት እና ዘላቂ ጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሀገራችን በቀጣይ በምትተገብረው ሪፎርምም የውሃ መስኩን ለማስተዳደር በተናበበና በዕውቀት ላይ በመመስረት ማስተዳደር እንደሚገባ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በላይነህ ይርዳው የዕለቱን ውይይት በይፋ በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል።
በዕለቱም የሀዋሳ ሀይቅን ለመጠበቅ ስትሪን ኮሚቴ የተቋቋመና ከዚህ ቀደም የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመ በመሆኑ እሱን ለመተግበር በዚህ መድረክ ደግሞ ስትሪንግ ኮሚቴ የተግባር መግባቢያ ሰነድ አወቃቀር፣ የስራ ድርሻና ተጠያቂነትን የያዘ ሰነድ ይዘት ለውይይት ቀደም ባሉ መድረኮች ለሂስ/ለግብዓት የቀረበ መሆኑን በማንሳት አሁን የተሰጡትን ግብአቶች በማካተት በዛሬው እለት ለማጸደቅ በድጋሚ ለስትሪንግ ኮሚቴው በቤዚን ጽ/ቤቱ ባለሙያ በአቶ ብርሀኑ ማኬቦ ቀርቧል።
በውይይት መድረኩም ከውኢሚ፣,ከመሬትናውሃ ሀብት ማዕከል፣ከኦሮሚያና ከሲዳማ ክልሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣በተፋሰሱ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የመንግስት የትምህርት ተቋማት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና በሀይቁ ዙርያ ያሉ ሆቴሎች (ሀይሌ ሪዞርት)ተገኝተዋል።
መድረኩንም መሬትና ውሃ ሀብት ማዕከል(WLRC)፣ GIZ እና የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች በጋራ አዘጋጅተዋል።
በቀጣይም ባለው መርሀ ግብር የሀዋሳ ንዑስ ተፍሰስ ኦዲት ሪፖርት፣ፍታዊ የውሃ አጠቃቀም ጥናት እንደሚቀርብ እንዲሁም የተግባር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስነስርዓት እንደሚኖር አቶ እስክንድር ፈለቀ የሀዋሳ ሀይቅ ደህንነት ጥበቃ እና የዝዋይ ሻላ/ደንበል ሻላ ን/ተፋሰስ የGIZ ፕሮጀክት ማናጀር እና የስ/ሸ/ሀ/ቤዚን አስተዳደር ዴስክ ሀላፊ አቶ አበበ አሰሌ ገልጸዋል።