የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተፋሰሱን ስነ ምህዳር በመጠበቅ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያግዛል ተባለ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተፋሰሱን ስነ ምህዳር በመጠበቅ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያግዛል ተባለ።

ሰኔ 28/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቤዚን አቅፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት /BaSRINET/ በኦሮሚያ ክልል ከምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ኢብሮ ሳዴን ቀበሌ ለተውጣጡ ሴቶች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተፋሰሱን ስነ ምህዳር በመጠበቅ የሴትችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያግዛል ተባለ።

በዋቢሸበሌ ቤዚን የባዘርኔት (BaSERINET) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኢሊያስ ሁሴን በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃግብር ላይ ለስልጠናው ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የበላይ አመራሩን፣ የምስራቅ ሀረርጌ ዞንና የባቢሌ ወረዳ አመራሮችን፣ አሰልጣኞችን እና ተሳታፊዎችን አመስግነው፤ ሴቶቹ ከስልጠናው ባሻገር በፉይናንስ ቢደገፉ የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ቢደረግላቸው የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ ኢሊያስ አክለውም ከኢፋዲ ቀበሌ የመጡት ሴቶች እና ሌሎችም ተሳታፊዎች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመተግበር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅምና የሥራ ፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ እንዲሁም በተቀናጀ የውሃ ሀብትና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱም አሳስበዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በንግድና በስራ ፈጠራ ላይ ለተሰማሩ ሴቶች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ መርሃግብር ላይ በቤዚን አቅፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተፋሰሱን ስነ ምህዳር በመጠበቅ የሴትችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያግዛል ያሉት አሰልጣኝ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ፅ/ቤት የስልጠና ክፍል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበበ ሰልጣኞቹ ከተፋሰስ ስራው ጎን ለጎን የራሳቸውን ገቢ ለማስገኘት በተሰማሩበት ዘርፍ ወጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ሌላኛው አሰልጣኝ አቶ ያሲን ሁመድ በበኩላቸው የአካባቢውን ሁኔታ በመቃኘት በወንዙ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ያለውን ዕድል ተጠቅመው ተፋሰሱን እያለሙና እየተንከባከቡ የስራ ዕድል ተፈጥሮራቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ስለሆነ ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ወደስራ እንዲገቡ የሚመለከተው አካል ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግም አሳስበዋል።

የተፋሰስ እንክብካቤ ስራዎችን ለመስራት የግድ ትላልቅ ወንዞች ዳርቻ ላይ መኖር አይጠበቅም ያሉት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከአስተዳደር ቢሮ ተሳታፊ የሆኑት ወ/ሮ እታገኘሁ ታደሰ ያገኙትን ስልጠና ለሌሎች ማጋራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በግብርና የሚተዳደሩት ወ/ሮ ሳህራ አህመድ ሙሜ እና ወ/ሮ ሀምሲያ ሙመድ ከማል ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት ከነበረን የአኗኗር ሁኔታ በተሻለ መልኩ ለመለወጥ ምንም እንኳን በተፋሰሱ አካባቢ ውሃ ያለው መሬት ቢኖረንም በቀጣይ የኃይል አቅርቦት ተመቻችቶልን በመስኖ መጠቀም ብንችል ተፋሰሱንም ለመጠበቅ ዝግጁ ነን ብለዋል።

Share this Post