የተለያዩ ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ወደ ስራ እንዲገባ ተወሰነ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ወደ ስራ እንዲገባ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19 ቀን 2018 (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ወደ ስራ እንዲገባ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው 5 ጉዳዮች መካከል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ደንብ ይገኝበታል።
በዚህም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቷል፡፡
ተቋማቱ ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች በውስጥ ገቢ የሚሸፈኑ ወጪዎችን ከአገልግሎት ተጠቃሚዎች በሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ለመሸፈን እንዲችሉ የአገልግሎት ተጠቃሚውን አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት በጥራት መስጠት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንዲያስችሉ ረቂቅ ደንቦቹ ተዘጋጅተው ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።