የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ተባለ።
የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ተባለ።
ሰኔ 07/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለማቋቋም በተዘጋጀ የውይይት ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ተባለ።
በአዳማ ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ላይ የውሃ ሀብታችንን በዘላቂነት ለማስተዳደር፣ ለማረጋገጥ እና የዜጎችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ተቋሙ ለከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለማቋቋም የተሰራው ጥናት ተጠናክሮ ለትግበራ እንዲበቃ አሳስበዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሀመድ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለማቋቋም የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር በውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ለውጥ ለማምጣት ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ትኩረት መሰጠቱን የገለፁት አቶ ኑረዲን መረጃዎችን በማደራጀትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
አቶ ኑረዲን አያይዘውም የውሃ አገልግሎት ተቋማት ላይ ለውጥ የሚያመጡ ተግባራትን በማከልና አዋጁን በማዳበር ወደትግበራ ለመግባት የክልሎችና የግሉን ዘርፍን ጨምሮ የሁሉም ጥረት ሊታከልበት ይገባል ነው ያሉት።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፋ በበኩላቸው ለህብረተሰቡ እየሰጠን ያለነው አገልግሎት በመንግስት ስታንዳርድ ነው የሚለውን የሚያሳይ እና የጋራ የሆነ ስታንዳርድ እንዲኖር፤ ክልሎችም እንደራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ሊተገብሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አዋጁ እውን እንዲሆን የሁላችንም ጥረት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ታምሩ የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱም ከ WaSH ጋር በማስተሳሰር ይሰራበታልም ብለዋል።
ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለማቋቋም በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከግል አማካሪ ድርጅት ጋር ለተከታታይ ቀናት ውይይት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ተቋሙ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የክልል ውሃ ቢሮ ኃላፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።