ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
ሰኔ3/2018ዓም(ወ.ኢ.ሚ)የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር UNDP/ብሄራዊ የቻይልድ ፕሮጀክት በአፍሪካ ሚኒ-ግሪድ ፕሮግራም በሚኒ-ግሪድ እና በታዳሽ ኃይል ልማት ባዘጋጀው ሥልጠና ላይ መንግስት ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየሠራ መሆኑ ተገልጸ።
መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች፣ አሰልጣኞችና አጋር አካላት በተዘጋጀ የሥልጠና ላይ መንግሥት ለሁሉም ዜጎች ፍትሐዊ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ በሰፊው እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የብሔራዊ ኤሌክትሪክ መስመር (Grid) ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች የታዳሽ ኃይል አማራጭ የኃይል አቅርቦትን ማድረስ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸው የሚኒ-ግሪድ ልማት ዘላቂና ውጤታማ እንዲሆን ቴክኖሎጂ ብቻውን በቂ እንዳልሆነና ምቹ ፖሊሲዎች፣ ዘላቂ የንግድ ሞዴሎች፣ የፋይናንስ አማራጮች፣ የአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም የጠነከረ ተቋማዊ አቅም እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።
ሥልጠናው በዘርፉ ቀጣይ ዕድገት ላይ ተፅዕኖ ባላቸው አምስት ዋና ዋና ነጥቦች ማለትም አማራጭ የአገልግሎት አቅርቦት ሞዴሎች፣የዋና ግሪድ መድረስ(Grid Arrival)፣የሚኒ-ግሪድ አስተዳደር ፣የኤሌክትሪክ ምርታማ አጠቃቀም፣ፋይናንስ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።
በመጨረሻም ሥልጠናው ዕውቀትን ለማጋራት፣ ልምዶችን ለመለዋወጥ እና የጋራ መፍትሔዎችን ለመፈለግ ጠቃሚ መድረክ መሆኑን ጠቁመው ተሳታፊዎች በንቃት በመሳተፍ ተግባራዊ የውሳኔ ሐሳቦችን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኤንዲፒ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ይመስላል ተፈራ ፕርጀክቱ የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እና ኢንቨስትመንትን መሳብ የሚያስችሉ አዳዲስ አቀራረቦችን በመመርመር የብሔራዊ ግሪድ መስፋፋት በሚቀጥልበት ወቅት ቀደም ብለው የተሰሩ የሚኒ-ግሪድ ኢንቨስትመንቶች እንዳይባክኑ እና የባለሀብቶች እምነት እንዲጠናከር ግልጽ አሠራሮችን መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የፀሐይ ፓነሎች ባትሪዎች እና ሌሎች መሣሪያዎች የአገልግሎት ዘመናቸው ሲያበቃ ለአካባቢ ጥበቃ በአግባቡ የሚወገዱበትን ሥርዓት ማዘጋጀት ፤የኃይል አቅርቦትን በግብርና፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በማምረት፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎች ላይ በማዋል የሥራ ዕድል ፈጠራንና የገቢ በማሻሻል የሕዝብና የግል ዘርፍ ፋይናንስን በማቀናጀት፣ የኢንቨስትመንት ስጋቶችን መቀነስ እና አዳዲስ የፋይናንስ መፍትሔዎችን ማስፋፋት ላይ ለማተኮር የሚረዳ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
በስልጠናው ላይ የፌደራልና የክልል ኢነርጃ ቢሮ ሀላፊዎች ፣አጋር ድሮጂቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።