የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የበጀት ዓመቱን የመጨረሻ የስራ ትግበራ ግምገማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካሂዷል።
የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የበጀት ዓመቱን የመጨረሻ የስራ ትግበራ ግምገማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካሂዷል።
ግንቦት 27/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የትግበራ ግምገማ አካሄደ።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የበጀት ዓመቱን የመጨረሻ የስራ ትግበራ ግምገማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አካሂዷል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ እንደገለጹት የውሃ ሃብት አስተዳደር ንዑስ የስራ ቡድን የውሃና ኢነርጂ ሴክተር ቡድን አካል የሆነና በውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ የሚሰሩትን ተግባራት ለማሳለጥ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከሴክተር ተቋማትና ሌሎች ስራውን ሊሰሩ በሚችሉ አጋር አካላት የተዋቀረ መሆኑን ተናግረዋል።
እንዲሁም ቡድኑ በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎችን የማስተባበር፣ የማቀናጀትና የማስተዳደር ኃላፊነት ያለውና በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ አካላት በትብብር የሚሰሩ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በጋራ የሚታቀዱበት፣ የተሰሩ ስራዎች የሚገመገሙበት፣ የተገኙ ውጤቶች የሚሻሻሉበትና እንዲሁም የቀጣይ ዓመት የስራ አቅጣጫዎች የሚተዋወቁበት ተግባርን የሚያከናውን ጭምርም ነው ተብሏል።
የዕለቱ መርሃ ግብር በበጀት ዓመቱ ውስጥ በአምስት ዙር እንዲካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ሲሆን በዕለቱ የተካሄደው የዓመቱ የመጨረሻ መድረክ እንደሆነም ተመልክቷል።
በመርሃ ግብሩ ከንዑስ የስራ ቡድኑ የተወከሉ አካላት የስራ ክንውን በዝርዝር ለውይይት የቀረበ ሲሆን በዘርፉ ቀደም ባሉ ጊዜያት የተሰሩ፣እየተከናወኑ ያሉና ወደፊት የሚከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ለቀጣይ ጊዜ የሚወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች ተገምግመው ዘርፉ በታቀደቀው መሠረት ግቡን እንዲመታ እገዛ የሚያደርጉና አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥሩ አስተያየቶችና ግብዓቶች ተወስደዋል።
በውይይቱ በውሃ ላይ ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጋር ቅንጅት ለማድረግ ፣አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመፍጠር ፣በአጋር አካላት እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ለመመርመርና የዘርፉን የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ለመደገፍ የሚቻልበትን መንገድ ለመፍጠር የሚያስችሉ ጉዳዮችም በስፋት ተነስተዋል።
በተለይም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አነሳሽነት እየተዘጋጀ ያለው የኢትዮጵያ የተፋሰስ መረጃ ስርዓት (Ethiopian Basin Information system) ለውይይት የቀረበ ሲሆን
በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች የዘመኑና የተቀላጠፉ እንዲሆኑ የሚያስችል በመሆኑ ይበል የሚያስብል መሆኑም በአጽንኦት ተመልክቷል።
በመድረኩ ከተነሱት ሃሳቦችና አስተያየቶችም በተፋሰሱ ምክር ቤት ለሚሰሩ ስራዎች እገዛ ለማድረግ የሚያስችል ቡድን እንዲኖርና በቀጣይ ለሚካሄደው የአጠቃላዩ የባለድርሻ አካላት ፎረም የሚቀርቡ ግብዓቶች ስለተገኙበት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፉን ለማሳደግ የሚችልባቸውን ምቹ መደላድሎች ይፈጥራልም ተብሏል።
ተሳታፊዎች በዘርፉ የተገኙ መሻሻሎችን በማድነቅ ቀሪ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በጋራ መስራት እና የተቋማት ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግም መክረዋል።
በመድረኩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ስራ አስፈጻሚዎች፣ የባዘርኔትና ብራይት ፕሮጀክት አስተባባሪዎች፣ ከአለም ባንክ፣ ከዴንማርክ፣ ኔዘርላንድና ከጣሊያን ኢምባሲ ተወካዮች፣ ከጀርመን የውሃ ባለስልጣን እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ወኪሎች ተሳትፈዋል።