የዋቢ-ሸበሌ ተፋሰስ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ገመገሙ።

የዋቢ-ሸበሌ ተፋሰስ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ገመገሙ።

ድሬደዋ ነሐሴ 11/2018ዓም(ው.ኢ.ሚ) ውይይቱን የመሩት የዋቢሸበሌ ቤዚን የባዘር ኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኤሊያስ ሁሴን ፕሮጀክቱ ይዞት ከተነሳው አምስት አላማ ማለትም የሃይድሮሎጂካል መረጃ ሥርዓት የመዘርጋት፣ ለቤት ውስጥና ለግብርና ፍላጎቶች በቂ የውሃ አቅርቦት ማረጋገጥእንዲሁም የጎርፍ አደጋ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተፅእኖዎች መቀነስ፣የመሬት መራቆትና ብክነት የሚያስከትሉትን ተፅዕኖዎች በመቀነስ ተጋላጭ የሆኑ የተመረጡ ተፋሰሶችን ማስተዳደርና መከላከያ ዞኖችን (buffer zone) መጠበቅ፣ለሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችናየቴክኒክ አስተዳደር እና የቁጥጥር አካላት አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ለተለያዩ የውሃ አጠቃቀም እና ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባራት የታዳሽ ሀይልን ከመጠቀም አኳያ የዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ ላይ አጠቃላይ የሆነ የሃይድሮሎጂካል ሥርዓት የመፍጠር እና የውሃና አስተዳደር ተደራሽነትን የማረጋገጥ ሥራዎች በትኩረት መዳሰሳቸውን ገልጸዋል ።

በተመሳሳይ ፕሮጀክቱ ለቤት ውስጥ እና ለግብርና ፍላጎቶች በቂ የውሃ አቅርቦት ለማረጋገጥ እንዲሁም የጎርፍ አደጋ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመቀነስ እየሰራ መሆኑም ጠቁመዋል።

​በተጨማሪም አቶ ኤሊያስ የመሬት መራቆት እና ብክለት የሚያስከትሉትን ተጽዕኖዎች ለመቀነስ፣ ተጋላጭ የሆኑ የተመረጡ ተፋሰሶችን ማስተዳደር፣ የተገነባ ዞን አስተዳደርን ማጠናከር እንዲሁም የመከላከያ ዞኖችን (buffer zones) የመጠበቅ ሥራዎች በስፋት መሠራታቸውን ገልጸዋል ።

​በመድረኩ ላይ የማስተባበር አቅምን የመጨመር ሥራዎችን በማጠናከር የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችን፣ የቴክኒክ፣ የአስተዳደር እና የቁጥጥር አካላትን አቅም ማጎልበት የማጎልበት ስራ መሠራቱን አብራርተዋል።

እንዲሁም ለተለያዩ የውሃ አጠቃቀም እና ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባራት የሚውሉ የሶላር (ታዳሽ) ኃይል ምንጮችን የማልማት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተብራርቷል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ደካማ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና ከእውነታው የራቁ የፕሮጀክት ተስፋዎች፣የግዢ መዘግየቶች፣ የርቀት ጣልቃገብነት ጣቢያዎች እና የሎጂስቲክስ ተግዳሮቶች፣የዋጋ ጭማሪ እና የተጋነነ የጨረታ ዋጋ፣የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ፣ዝናብ ዘግይቶ መቆየቱ የተክሎች እንቅስቃሴ እንዲቀንስ አድርጓል እና ሌሎች ተመሳሳይ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተገልጿል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋቢ ሸበሌ ቤዚህን በበኩሉ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ትኩረት በመስጠት ሰው በመመደብ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን በማሳደግ እና ጣልቃገብነቶችን ከተመሳሳይ IWRM ፕሮጀክቶች ጋር በማጣጣም የባለድርሻ አካላትን ትብብር በማጠናከር፣ቀጣይነት ያለው ክትትል እና አስተዳደራዊ ድጋፍ፣ውሳኔዎችን ለማፋጠን የከፍተኛ አመራር ተሳትፎ በማጠናከር ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ማድረጉን ገልጿል ።

የቴክናክ ኮሚቴው በቀረበለት የእቅድ አፈፃፀም በመነሳት ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ ስራው የታለመለትን ግብ እንዲመታ የታዩ ጉድለቶች በተለይ ከግዥ ጋር የነቀሩ ክፍተቶች ተሟልተው ተጠናክረን በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post