የከተሞችን የሳኒቴሽን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ሻሸመኔ # መጋቢት 17/2018 ዓ/ም ውኢሚ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሳኒቴሽን መሠረተ ልማት መሪ ስራአስፈጻሚ የከተሞችን የሳኒቴሽን ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዝ "operation & maintenance of treatmentpl plant" በሚል ርዕስ ለተመረጡ የክልል የውሃ ቢሮዎች እና ለከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎች ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው የተዘጋጀው እንደ ሀገር ከተሞችን ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ያለውን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን በተወሰኑ ከተሞች ዘመናዊ ፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት /Faecal sludge treatment plant / ግንባታው ወደ መጠናቀቅ እየደረሰ በመሆኑ ለባለሙያዎችና ሀላፊዎች የትግበራና የጥገና /operation & maintenance /ግንዛቤ መጨበጥ ስላለባቸው ነው።
የስልጠናውን መርሃግብር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የሳኒቴሽን መሠረተልማት መሪ ስራአስፈፃሚ አቶ ኑረዲን መሐመድ እንደ ሀገር የሳኒቴሽን ሁኔታ በጅምር ደረጃ ያለ በመሆኑ ሁሉም የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ የታቀደውን ስራ ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ ውጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል።
ስልጠናው የሚያተኩረው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የከተማ ዘመናዊ ፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ / Faecal sludge treatment plant / ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የጋራና የህዝብ መፀዳጃዎች ትግበራና ጥገና ላይ በመሆኑ ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ አደራ ብለዋል።
አቶ ኑረዲን አክለው ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የከተማ ዘመናዊ ፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ / Faecal sludge treatment plant / ከፍተኛ ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት የፈሰሰበት ፕሮጀክት በመሆኑ የቀሩ ስራዎች በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ትግበራ ለመግባት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ከስልጠናው በሚያገኙት ዕውቀትና ግንዛቤ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ከህንድ ሀገር ስልጠናውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው የመጡትን አሰልጣኞች አመስግነው ሰልጣኞች በጥያቄና መልስ፣ ግልጽ የልሆኑ ጉዳዮችን በመጠየቅና ቀና ሀሳቦችን በማዋጣት ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉና እንዲሳተፉ አቶ ኑረዲን ተማጽነዋል።
ከሀገረ ህንድ የመጡ አሰልጣኞችም በበኩላቸው በሳኒቴሽን ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር የመስራት ዕድል በማግኘታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው ስልጠናው በከተማ ዘመናዊ ፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ / Faecal sludge treatment plant / ፕሮጀክት ትግበራና ጥገና /operation & maintenance of treatmentpl plant" ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ስለሚያተኩር ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው መከታተልና መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በተለያየ ክፍል /session /የተከፋፈለ ሰፈፊ ጉዳዮችን የያዙ ሰነዶችንም ለሰልጣኞች በጽሑፍ አቅርበዋል።
ሰልጣኞችም በቀረበው የስልጠና ሰነድ ላይ በቡድን ውይይት፣ በጥያቄና መልስ እና በፕሮጀክቶች ትግበራና ጥገና ዙሪያ ያላቸውን ልምድ በማካፈል ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል።