2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮችና የግል ድርጅቶች ዕውቅና በመስጠት ተጠናቀቀ።

2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮችና የግል ድርጅቶች ዕውቅና በመስጠት ተጠናቀቀ።   ጥቅምት 21/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው 2ኛው የውሃና ኢነርጂ ሳምንትን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ተዘጋጅቶ በነበረው አውደ ርዕይ ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የልማት አጋሮችና እና የግል ድርጅቶች እውቅና ተሰጠ።   ዕውቅናውን የሰጡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ አውደ ርዕዩ በውሃውና ኢነርጂው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ እንደነበር ገልጸዋል።   በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ለተከታታይ 5ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ለተሳተፋ የልማት አጋሮች እና የግል ድርጅቶች እንዲሁም በፋይናንስ ላገዙ አጋር ድርጅቶች፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኬኒያ እና ከቻይና ለተሳተፉ እንዲሁም ለፕግራሙ ፓናሊስቶች ሁሉ ክቡር ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።   ሁነቱ ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮች፣ ለግል ድርጅቶች እና የሚዲያ አካላት እውቅና በመስጠት ተጠናቋል።

Share this Post