የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከSNV ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የብሔራዊ ባዮ ጋዝ ፕሮግራም 9848 የደንበኞች ጥሪ ማዕከልን በይፋ አስመረቀ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከSNV ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የብሔራዊ ባዮ ጋዝ ፕሮግራም 9848 የደንበኞች ጥሪ ማዕከልን በይፋ አስመረቀ፡፡ ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርከ SNV ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የብሔራዊ ባዮ ጋዝ ፕሮግራም 9848 የደንበኞች ጥሪ ማዕከልን በይፋ አስመረቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብሔራዊ የባዩ ጋዝ ፕሮግራምን ተግባራዊ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ከ50 ሺ የባዮጋዝ ፕላንት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ይህንን ፕሮግራም በማስፋፋት የማህበረሰቡን የባዮጋዝ ተጠቃሚነት የበለጠ ለማስፋፋት እና ችግሮችን ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከSNV ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 9848 የደንበኞች የነጻ ጥሪ ማዕከልን በዛሬው እለት በይፋ አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ይህ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ከአሁን በፊት በወኪል አማካኝነት ሲሰራበት የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለቤትነቱን ወስዶ የሚተገብረው ሲሆን ለባዮ ጋዝ ፕሮግራም ብቻም ሳይሆን ለሶላር ኢነርጂ እና ለሌሎች የተቋማችን ተግባራት የምንጠቀምበት የነጻ ጥሪ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ብለዋል፡፡ ይህ የነጻ የጥሪ ማዕከል በባዮ ጋዝ ማብለያው ዙሪያ ክትትል ለማድረግ፣ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት፣ ለተጠቃሚዎች ስለቴክኖሎጅው መረጃና ምክር ለመለገስ እንዲሁም አዳዲስ የቴክኖሎጅ ፈላጊዎችን ለመቀበልና ለመመዝገብ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት መረጃ መስጠትም መቀበልም የሚቻልበት ቴክኖሎጅ ነው ሲሉ የባዮጋዝ ፕሮግራም ማናጀሩ አቶ ተመስገን ተፈራ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ቴክኖሎጅው በተለያዩ ቋንቋዎች መረጃን መለዋወጥ ያስችላል ያሉት ማናጀሩ በዋናነት አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛና የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጅዎች በስፋት በተገነቡባቸው አካባቢ ያሉ ቋንቋችን ማዕከል በማድረግ የሚተገበር ይሆናል ብለዋል፡፡ በእለቱ የብሔዊ ባዮጋዝ ፕሮግራም ፎካልን ጨምሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር ከSNV ኢትዮጵያ፣ ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የመጡ የባዮጋዝ የስትሪግ ኮሚቴ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Share this Post