የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተቀማጭነቱ በሀገረ አሜሪካ ከሆነው የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስስ (Catholic Releif Services CRS) ፕሬዘዳንት እና ዋና ሥራ አስፍፃሚ ጋር ውይይት አደረገ፡፡
ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ( ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ከካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ፕሬዘዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሾን ካሉን (Mr. sean L. callahun) ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት በሚስቴር መስሪያ ቤቱ ሶስት የዘርፍ አደረጃጀት እንዳለና ይኸውም የመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ዘርፍ ፤ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ እና የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ተብለው እንደሚከፈሉ አስገንዝበዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በእያንዳንዱ ዘርፍ CRS ለሚያደርገው ድጋፍና ትብብር በመስሪያ ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው ወደ ፊትም በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አክለውም ከለውጡ በኋላ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ነገር ግን የተሰራው ስራ ካለው ፍላጎት አንፃር በቂ ስላልሆነ በትብብር በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር ሚኒስቴሩ CRS ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር እየሰራ ያለው ሰራ በመጠጥ ውሃው ዘርፍ ላለው ለውጥ አጋዥ እና ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገበ በመሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ ትብብሮችና ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ ፕሬዘዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ Mr. sean L. callahun ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዓመታት ከድርጅታቸው ጋር በትብብር እና በቅንጅት እየሰራ ላለው ስራ ትልቅ ምስጋና አቅርበው ወደ ፊትም ይኸው ትብበር በሚገባ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ወቅት ገልፀዋል፡፡
CRS በኢትዮጵያ ውስጥ በመጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ከሚንቀሳቀሱ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ከሚኒስቴር መ/ቤታችን ጋር በቅርበት ከሚሰሩ እና ውጤታማ ፕሮጀክቶችን ከሚተገብሩ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡
በውይይቱ የሚኒስቴር መ/ቤቱ አማካሪዎች የሲ አር ኤስ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡